Ethiopian Railways Corporation

አዲስ -ጅቡቲ የባቡር መስመር

ኢትዮጵያ በእድገት እና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ከያዘቻቸው ትላልቅ ፕሮጀክቶች የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመር አንዱ ነው፡፡ በኤሌክትሪክ ሀይል የሚሰራው ከአየር ብክለት ነፃ የሆነው ይህ የባቡር መስመር 656 ኪ.ሜ ርዝመት አለው፡፡

የአዲስ አበባ – ጅቡቲ የባቡር መስመር የቻይና መንግስት ባለቤት የሆኑ ሁለት ኩባንያዎች ማለትም የቻይና የባቡር መስመር ግሩፕ (CREC) እና የቻይና ሲቪል ኢንጂነሪንግ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን (CCECC) ግንባታው 2005 ዓ.ም ተጀምሮ በ2010 ዓ.ም የግንባታ ሂደቱ ተጠናቆ ለአገልግሎት በቅቷል፡፡

የባቡር መስመሩ የተገነባው ከቻይናው ኤግዚም ባንክ (EXIM Bank) በተገኘ 4 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ብድር ሲሆን ግንባታው የተከናወነው በ(EPC Turnkey) ውል ነው፡፡ የቻይና አለምአቀፍ የምህንድስና አማካሪ ኮርፖሬሽን (CIECC) በአማካሪነት እና በተቆጣጣሪነት ሰርቷል፡፡ የባቡር ሐዲዱ 19 ጣቢያዎች ያሉበት ሲሆን በሰዓት 120 ኪሎ ሜትር የመጓዝ አቅም አለው፡፡

 

የባቡር ሐዲዱ 19 ጣቢያዎች ያሉበት ሲሆን በሰዓት 120 ኪሎ ሜትር የመጓዝ አቅም አለው፡፡

How can we help you?

Contact us at the Ethiopisn Railway Corporation Headoffice or submit a business inquiry online