የአዋሽ - ወልድያ ፕሮጀክት
የአዋሽ – ወልዲያ/ሀራ ገበያ/ ፕሮጀክት 392 ኪ.ሜ ርዝመት እና 1.435 ሜ ስታንዳርድ አለው፡፡ ባለአንድ ነጠላ ሀዲድ ሲሆን ከ15 በላይ ጣቢያዎች ይኖሩታል፡፡ አዋሽ ፣አርማንያ፤ከሚሴ፣ሃይቅ እና ሀራ ገበያ በዚህ መስመር /ኮሪደር/ ላይ ከሚያቋርጡ ጣቢያዎች መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
በአጠቃላይ የፕሮጀክቱ ሥራ 33.34% ደርሷል፡፡ ይህ ከምስራቅ ወደ ምዕራብ የተዘረጋው የአፍሪካ ምድር ባቡር መረብ አካል ሆነው መስመር ዝርጋታው ተጠናቆ ስራ ሲጀምርም ወደ ጅቡቲ በሚደረገው ጉዞ የሚወስደውን ጊዜ ከ50 በመቶ በላይ ይቀንሳል፡፡ ለመካከለኛ የኢትዮጵያ ክፍል የኢኮኖሚ ዕድገትም ትልቅ አስተዋፅኦ ይኖረዋል፡፡
የአክሰስ (መጋቢ) መንገድ ግንባታ፣ የባችንግ ፕሊንት ተከላ ስራ፣ የክሬሸር ተከላ፣ የወርክ ሾፕ ግንባታ፣ የዋሻ ጥልቅ ጥናት፣ የዋሻ ቁፋሮ፣ ስቶን ፒቺንግ፣ የአፈር ቆረጣና ሙሊት ስራ 13,780,117 ሜትር ኩብ ተከናውነዋል፡፡
በተጨማሪም 1000 (አንድ ሺህ) ተሸከርካሪዎችና ማሽኖች ተገዝተው በመጓጓዝ ላይ ሲሆኑ 500 ማሽኖችና ተሸከርካሪዎች ገብተው በስራ ላይ ይገኛሉ።
ሁለት ዋና ዋና እና 8 ጊዜያዊ የመኖሪያ ካምፖች በተለያዩ አካባቢዎች ተገንብተዋል በተጨማሪም የዎርክ ሾፕ ግንባታ ኮምቦልቻ ላይ ተጀምሯል።
የዲዛይንና ቴክኒካል ስራዎች (Design & Technical)፤የቅድመ ግንባታ (Mobilization)፤አፈር ቆረጣ እና ሙሊት ስራ (Sub-grade Works)፤የሲቪል (Civil Structure)፤የትራክ (Track Works)፤የኤሌክትሪክ እና ሃይል አቅርቦት ፤የስቴሽን ህንፃዎች ግንባታ፤የድልድይና ቪያደክት ፤የዋሻ ቁፋሮ (Tunnel) እንዲሁም የማጓጓዝ ሥራዎች (Transportation Works)
በአጠቃላይ የፕሮጀክቱ ሥራ 33.34% ደርሷል፡፡
How can we help you?
Contact us at the Ethiopisn Railway Corporation Headoffice or submit a business inquiry online