Ethiopian Railways Corporation

የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን “ኢትዮጵያ ትገነባለች ፈጠራ፣ፍጥነት እና ጥራት ለመሠረተልማት እመርታ በሚል መሪ ሀሳብ ከሚያዝያ 9-12/2018 ዓ.ም በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽል ማዕከል እየተካሄደ ባለው የመሠረተ ልማት እና የኮንስትራክሽን ሳምንት ላይ እየተሳፈተ ይገኛል፡፡

አውደ ርዕዩን በይፋ የከፈቱት የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ባስተላለፉት መልዕክት፤ መሠረተ ልማት ለሀገር ዕድገት ወሳኝ ግብዓቶችን በማመላለስ ረገድ የኢኮኖሚው የደም ሥር እና የብልጽግና መሠረት መሆኑን ገልጸዋል። ባለፉት ዓመታት በመንገድ፣ በባቡር፣ በኃይልና በዲጂታል ዘርፎች የተመዘገቡ ተጨባጭ ስኬቶች የሀገሪቱን የልማት ጉዞና የወደፊት ተስፋ የሚያንፀባርቁ መሆኑንም አክለዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አያይዘውም፣ በአውደ ርዕዩ ላይ የተመለከቷቸው ወሳኝ የልማት ተቋማት መሠረተ ልማትን በቅንጅትና በትብብር የመምራት አዲስ የሥራ ባህል እየገነቡ መሆኑን አድንቀዋል። በተለይም የትራንስፖርት ትስስርን በማሳለጥ ረገድ የባቡር መስመሮችና የሎጅስቲክስ ማዕከላት ለሀገሪቱ የወጪና ገቢ ንግድ ያላቸውን ፋይዳ አጉልተዋል።

መንግሥት የዜጎችን የሥራ ዕድል የሚያሰፉና የኢኮኖሚውን መዋቅር የሚቀይሩ እንደ ኮሪደር ልማትና ታዳሽ ኃይል ያሉ ፕሮጀክቶችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል በመግለጽ፤ አሁን ያለንበት ወቅት የሥራ፣ የውጤትና የተስፋ ዘመን መሆኑን አቶ ተመስገን አረጋግጠዋል።

የከተማ መሰረተ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ በበኩላቸው ዛሬ የተከፈተው የመሰረተ ልማትና ኮንስትራክሽን ሳምንት የአገራችንን ብልፅግና የምንመዝንበት እና የዘርፉን ቀጣይ ዕድገት የሚያመላከት ስትራቴጂ የሚቀመጥበት መሆኑን ገልፀዋል፡፡

 

ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፤

ፌስቡክ፡  https://www.facebook.com/…/Ethiopian-Railways…/
ቴሌግራምhttps://t.me/EthiopianRailwaysCorporati
ድረ  ገፃችንንም ይጎብኙ:  www.erc.gov.et