Ethiopian Railways Corporation

Train Master (የባቡር ካፒቴን) መሆን ይፈልጋሉ? ወይንስ

በዘመናዊ ባቡር መሰረተ ልማት ጥገና  እና ግንባታ ላይ ባለሙያ መሆን ይፈልጋሉ?

የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን—የባቡር ኢንስቲትዩት ከ ኢፌዲሪ ትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን ፍቃድ ባገኘባቸው ሶስት የቴክኒክና የሙያ ዘርፎች ለ2019 ዓ.ም የስልጠና መርሃ ግብር የሰልጣኞች ምዝገባ በይፋ መጀመሩን ያበስራል ።

ለዚህ ዓመት ሰልጣኞች በተለዩ የስልጠና

መርሀ ግብሮች ማለትም

በTrain Driving (Level 2 to Level 5),

Rolling Stock Electrical & Electronics System Maintenance (Level 2 to level 5),

Railway Signal & Communication System Installation and Maintenance (Level 1 to 5)

የመግቢያ መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾችን ተቀብሎ ማሰልጠን ይፈልጋል፡፡

በሁሉም የተለዩ የስልጠና መርሀ ግብሮች የሚመዘገቡ ሰልጣኞች በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መስፈርት መሠረት የ12ኛ ክፍል የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና መግቢያ ውጤት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

ሰልጣኞች ለባቡር ካፒቴንነት (Train Driving) ሙያ ስልጠና ለመመዝገብ በልዩ ሁኔታ የተረጋገጠ የሕክምናና የአካላዊ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

ለምዝገባ ሲመጡ ኦርጅናል የትምህርት ማስረጃዎንና ፎቶ ኮፒ ፣ የፋይዳ ዲጂታል ወይንም የቀበሌ ነዋሪነት መታወቂያ እና አራት ፓስፖርት ሳይዝ ፎቶግራፍ ይዘው መምጣት ይኖርቦታል።

ምዝገባ መካሄድ የሚጀመርበት ቀን ከጥቅምት16/2019 እስከ ጥቅምት 27//2019 ዓ.ም ብቻ ይሆናል።

አድራሻችን አያት ደራርቱ አደባባይ፣ የባቡር ኢንስቲትዩት የስልጠና ማዕከል።

ስልክ 011 6 390409 /011 4 702047

ያለን ቦታ እጅግ ውስን በመሆኑ ይሕ በአይነቱ ልዩ ዕድል እንዳያመልጥዎ ዛሬውኑ ይመዝገቡ ፤ የነገ የተስፋ ጉዞዎን አንድ ብለው ከአንጋፋው የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ጋር ይጀምሩ!

 

ለዘመነ እድገትና ትስስር፣

የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ባቡር ኢንስቲትዩት!

 

ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፤

ፌስቡክ፡  https://www.facebook.com/…/Ethiopian-Railways…/
ቴሌግራም:  https://t.me/EthiopianRailwaysCorporati
ድረ  ገፃችንንም ይጎብኙ:  www.erc.gov.et