Ethiopian Railways Corporation

“የውስጥ ኦዲት ሥራዎች የISO/IMS ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን በሚያሟላ አግባብ መከናወን ይኖርባቸዋል” ሲሉ የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ህሊና በላቸው አሳሰቡ።

ኮርፖሬሽኑ የ2019 ዓ.ም. የመጀመሪያ መደበኛ የማኔጅመንት ስብሰባውን  አካሂዷል።

ኮርፖሬሽኑ የISO ዓለም አቀፍ ደረጃዎች የእውቅና ሰርተፊኬት  ለማግኘት የሚያደርገው ጥረት በውስጥ ኦዲት ሥራዎች ላይም መንጸባረቅ እንዳለበት ኢንጂነር ህሊና ገልጸዋል። የኮርፖሬሽኑ የውስጥ ኦዲት ሥራ  የውጭ ኦዲት ሥራን ለማገዝ በሚያስችል አግባብ  ከተቀናጀ የአስተዳደር ሥርዓት (Integrated Management System—IMS) መርሆች ጋር በተጣጣመ መልኩ መከናወን እንዳለበት አስገንዝበዋል።

የውስጥ ኦዲት ሥራዎች በተገቢው መመሪያ፣ በማስረጃ ላይ በተመሠረተ ግምገማና በተጠያቂነት እንዲመሩ በስብሰባው ላይ ተጠቁሟል። ይህም ኮርፖሬሽኑ የISO/IMS ሰርተፊኬት ለማግኘት እያደረገ ላለው ዝግጅት  የውስጥ ቁጥጥርና የአፈጻጸም ማሻሻያ ሥራዎችን በማጠናከር ሂደቱን የሚያፋጥን  ነው።

በስብሰባው ላይ የውስጥ ኦዲት ቻርተር ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ (ኤአይ ኤች) በተሰጠው የሥራ መመሪያ መሰረት ለማኔጅመንቱ ቀርቧል። በዚሁ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት  ሆልዲንግ የሥራ መመሪያ ላይ ማዕከል ያደረገ ለቀጣይ የኮርፖሬሽኑ ሥራዎች የአፈጻጸም ማሻሻያ የሚሆን የሥራ አቅጣጫ መመሪያ በዋና ሥራ አስፈጻሚ በኩል ተሰጥቷል ።

የውስጥ ኦዲት ሥራዎች ዘወትር በጥራት፣ በተጠያቂነትና ቀጣይነት ባለው የመሻሻል መርሆች ላይ ብቻ እንዲመሠረቱም ተጠይቋል።

ከኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት !ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፤

ፌስቡክ፡  https://www.facebook.com/…/Ethiopian-Railways…/
ቴሌግራም:  https://t.me/EthiopianRailwaysCorporati
ድረ  ገፃችንንም ይጎብኙ:  www.erc.gov.et