Ethiopian Railways Corporation

ቋንቋ

አዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት

የከተማዋን የትራንስፖርት እጥረት ለማቃለል በመጀመሪያው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ተገንብቶ አገልግሎት የጀመረው የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንዚት አገልግሎት CREC (China Railway Group Limited) ከተባለ የቻይና ኩባንያ ጋር EPC/Turnkey/ የግንባታ ስምምነት ተፈራሞ ጥር 23 ቀን 2003 ዓ.ም የግንባታ ስራውን ጀመረ፡፡

በ475 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የተገነባ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 85% የቻይና የገቢ-ወጪ ባንክ (China EXIM bank) በብድር የተገኘ 15% በኢትዮጵያ መንግስት የተሸፈነ ነው፡፡ ይህ የባቡር መስመር 34 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው በሁለት አቅጣጫዎች የሚጓዝ፤ የምስራቅ -ምዕራብ መነሻ ከአያት አደባባይ መዳረሻው ጦር ሀይሎች ሆስፒታል ሲሆን 17.4 ኪ.ሜ ርዝመት አለው፡፡

የሰሜን-ደቡብ መስመር መነሻ ከዳግማዊ ሚኒሊክ አደባባይ መዳረሻው ቃሊቲ ሲሆን 16.59 ኪ.ሜ ርዝመት አለው፡፡ ሁለቱ መስመሮች ከመስቀል አደባባይ እስከ ልደታ ቤተክርስቲያን 2.7 ኪ.ሜ የጋራ ሀዲድ ይጠቀማሉ፡፡

የቻይና ስታንዳርድ ጌጅ 1.435 ሚ.ሜ ስፋት ያለው ባለ ሁለት ሀዲድ በመሬት፤በዋሻ ውስጥ እና በድልድይ የሚጓዝ ሲሆን የእግረኛ እና የመኪና ማቋረጫዎች አሉት፡፡

የዲዛይን ፍጥነቱ 80 ኪ.ሜ በሰዓት የኦፕሬሽን ፍጥነቱ ደግሞ 70 ኪ.ሜ ነው፡፡ 39 የመሳፈሪያ እና መውረጃ ጣቢያዎች ያሉት ሲሆን 27 በመሬት ላይ 9 በድልድይ ላይ 2 በከፊል ድልድይ እንዲሁም አንድ በዋሻ የሚገኙ ጣቢያዎችን ይዟል፡፡

39 የትኬት መቁረጫ ቢሮዎች፣ 18 የኃይል መቀበያ ጣቢያዎች፣ 22 ሊፍቶች እና 12 እስካሌተሮች ያሉት ሲሆን ለ18 ሰዓታት በሦት ፈረቃ አገልግሎት ይሰጣል::

በ2008 ዓ.ም መጀመሪያ የኦኘሬሽን ስራውን በይፋ የጀመረው የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንዚት አገልግሎት ሸን ዘን ሜትሮ ግሩፕ የተባለ የቻይና ኩባንያ ለ3 አመታት የማስተዳደር እና ጥገና ውል ስራ/ኮንትራት/ሰርተዋል፡፡ አንድ ነጠላ ባቡር በአንድ ጊዜ 317 መንገደኞች ማጓጓዝ የሚችል ሲሆን በአጠቃላይ 41 ባቡሮች ይገኛሉ፡፡

How can we help you?

Contact us at the Ethiopisn Railway Corporation Headoffice or submit a business inquiry online