Ethiopian Railways Corporation

አዋሽ-ኮምቦልቻ ወልዲያ ሀራ -ገበያ የባቡር ፕሮጀክት

የአዋሽ-ኮምቦልቻ ወልዲያ ሀራ -ገበያ የባቡር ፕሮጀክት በ2007 ዓ.ም ግንባታውን የጀመረ ሲሆን የባቡር መስመሩ 392 ኪ.ሜ የሚረዝም ሲሆን የሥራ ተቋራጩ ያፒ መርከዚ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን በተባለ የቱርክ ኩባንያ በ1.7 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ወጪ እየተገነባ ያለ ኘሮጀክት ሲሆን የማማከር ስራውን ደግሞ የፈረንሳዩ ሲስትራ መልቲ ዲ በተባለ አማካሪ ድርጅት እየተከናወነ ይገኛል፡፡

 10 ጣቢያዎች፤10 ኪ.ሜ ርዝመት ያላቸው 12 ዋሻዎች፤52 የተለያዩ ርዝመት ያላቸው ድልድዮች፤ 8 የሀይል መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች፤(ሰብስቴሽንስ)፤12 የሬዲዮ ምሰሶዎች፤ አንድ የጥገና ማእከል አሉት፡፡

በኤሌክትሪክ ሀይል የሚሰራ ከአየር ብክለት ነፃ የሆነ የመሀል እና የሰሜን ኢትዮጵያ ክፍሎችን የሚያስተሳስር መስመር ሲሆን የባቡር መስመሩ በሰዓት 120 ኪሎ ሜትር የማመላለስ አቅም አለው፡፡

How can we help you?

Contact us at the Ethiopisn Railway Corporation Headoffice or submit a business inquiry online