ወልዲያ -መቐለ ፕሮጀክት
የወልዲያ/ሃራገበያ- መቐለ የባቡር ፕሮጀክት ግንባታው የተጀመረው በ2007 ዓ.ም ሲሆን 1.6 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር በጀት ተመድቦለታል፡፡ የባቡር መስመሩ 216 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው ሲሆን ባለ አንድ ነጠላ ሃዲድ እና 1.435 ሜትር ስታንዳርድ ጌጅ ስፋት ያለውና ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰራ ነው፡፡
የሥራ ተቋራጩ የቻይና ኮሙዩኒኬሽን ኮንስትራክሽን ድርጅት (CCCC) ሲሆን የቻይና አለምአቀፍ ምህንድስና አማካሪ ኮርፖሬሽን (CIECC) በአማካሪነት እየሰራ ይገኛል፡፡
ፕሮጀክቱ 76 ድልድዮች፣ 370 የውሃ ማፋሰሻዎች እና አጠቃላይ 10.03 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያላቸው ስምንት 8 ዋሻዎች አሉት፡፡ በፕሮጀክቱ ካሉት ዋሻዎች መካከል ትልቁ 3.662 ኪሜ ርዝመት ያለው ነው፡፡
የባቡር መስመሩ ከወልድያ/ሃራ ገበያ ተነስቶ በሰሜን የሀገራችን ክፍል የሚገኙ ከተሞችን አቋርጦ ደረቅ ወደብ ያላትን መቐለ ከተማን መዳረሻው ያደርጋል፡፡ ፕሮጀክቱ የተለያዩ ከተሞችን አቋርጦ የሚያልፍ በመሆኑ የህብረተሰቡን ማህበራዊ ትስስር ለማጠናከር እንዲሁም ለከተሞቹ እድገትና ኢኮኖሚያ ተጠቃሚነት ጉልህ ሚና ይኖረዋል፡፡
How can we help you?
Contact us at the Ethiopisn Railway Corporation Headoffice or submit a business inquiry online