Ethiopian Railways Corporation

 

መስከረም 28/2ዐ16 ዓ.ም (ኢምባኮ)
በኮርፖሬሽኑ እየተጠና ባለው የManagement Information System (MIS) ፕሮጀክት ውስጥ ካሉት ሰነዶች/Modules/መካከል የቋሚ ንብረት ምዝገባ ስልጠና ለባለሙዎች መስከረም 28 ቀን 2016 ዓ.ም በአይ.ሲ.ቲ. ስልጠና ማእከል ተጀመረ፡፡

በኮርፖሬሽኑ የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ እና ሰነድ መምሪያ ኃላፊ አቶ ዮሃንስ ተስፋዬ ስልጠናው ያስፈለገበት ምክንያት በኮርፖሬሽኑ ያሉ ንብረቶችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ አደራጅቶ ለማስቀመጥ እና ምን ያህል ቋሚ ንብረት እንዳለ ለማወቅ፤ የምዝገባ ድግግሞሽን ለማስቀረት፤ በእርጅና ምክንያት ተቀናሽ የሆኑትን ለመለየት መሆኑን ገልጸው አገልግሎቱም ፈጣን እንዲሆን የሚያግዝ ነው ብለዋል፡፡
ስልጠናው ለአምስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን ለፋይናንስ፤ለምህንድስና መምሪያ ፤ለንብረት አስተዳደር እና ለኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ የስራ ክፍሎች ቀጥታ ከስራው ጋር ግንኙነት ያላቸው ባለሙያዎች ተመድበው እየለጠኑ ይገኛሉ፡፡

ከስልጠና በኋላ የኮርፖሬሽኑ የንብረት አያያዝ አሰራሩን የተከተለ እና ዘመናዊ በሆነ መልኩ የሚደራጅ መሆኑንና ለዚህም ባለሙያዎቹ ወደ ትግበራ ሲገቡ ድጋፍ እና ክትትል የሚያደርግ የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያ አስፈላጊ በመሆኑ በስልጠናው እንዲሳተፍ መደረጉን ለማወቅ ተችሏል፡፡
===========================



Leave a Reply