- November 13, 2023
- Posted by: Tigist desalgn
- Category: ዜና
No Comments
የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ባቡር አካዳሚ ዘርፍ ከኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት አስተዳደር ስልጠና በግዮን ሆቴል እየተሰጠ ይገኛል፡፡
የስልጠናው ዓላማ ኮርፖሬሽኑ በአሁኑ ወቅት የስትራቴጂ ለውጥ አድርጎ እየጀመራቸው ያሉ ፕሮጀክቶች እና የቢዝነስ ዩኒት ስራዎች ላይ አቅም በማሳደግ በቀጣይ ለሚሰራቸው ፕሮጀክቶች ተወዳዳሪ በመሆን አዲስ እይታ መፍጠር የሚያስችል ግንዘቤ ለማሳደግ መሆኑን የኮርፖሬሽኑ የባቡር አካዳሚ ዘርፍ ትምህርትና ስልጠና መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ሲሳይ ጉታ ገልፀዋል፡፡
ስልጠናው በፕሮጀክት አስተዳደር፤ የተወዳደሪ ኮንትራክተር መስፈርቶች፤ የዶክመንት ትግበራ ማዕቀፉ ፤ የፕሮጀክት ኮንትራት ውል መለኪያዎች እንዲሁም የፕሮጀክት ሂደት በሚሉ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ይዘት ያለው መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ስልጠናው ከጥቅምት 29 -30 /2016 ዓ.ም የሚሰጥ ሲሆን ተሳታፊዎቹም በዋናነት የሲቪል መሐንዲሶችና ሙያው በቀጥታ የሚመለከታቸው የቢዝነስ ዩኒት ባለሙያዎች ፤ ከወልድያ መቐለ ፕሮጀክት፣ አዋሽ-ኮምቦልቻ/ሀራ ገበያ ፕሮጀክት እና ከዋና መስሪያ ቤት የተውጣጡ እንደሆኑ ወ/ሮ ሲሳይ ገልፀዋል፡:
===========================