Ethiopian Railways Corporation

ኢምባኮ ህዳር 25/03/2016 ዓ.ም

የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን በዋና መስሪያ ቤቱ ለሚያስገነባው ሁለገብ ማዕከል ህንፃ እየተጠና ባለው ዲዛይን ላይ ከኮርፖሬሽኑ የስራ ኃላፊዎችና የጥናት ቡድን ጋር ህዳር 25 ቀን 2016 ዓም በኮርሬሽኑ የስብሰባ አዳራሽ ውይይት አካሄደ፡፡

ጥናቱ የተዘጋጀው China Rail Transit Engineering Consultancy (CRTEC) በተባለ አማካሪ ድርጅት የተዘጋጀ ሲሆን የዲዛይን፣ የቴክኒክ እና የፋይናንስ ፍላጎት በዝርዝር ቀርቧል፡፡

የዲዛይን ጥናቱ የተቋሙን ዋና መስሪያ ቤት ጨምሮ መኖሪያ ቤት፣የንግድ ማዕከል፣ሆቴል እና የመዝናኛ ስፍራዎችን ያካተተ ሲሆን ከዚህ በፊት የተሰጡ አስተያየቶችን በግብዓትነት ተጠቅሞ ተሻሽሎ የተሰራ ነው፡፡
የውይይቱ ተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች አቅርበው በአማካሪ ድርጅቱ ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡

 

 

 

 



Leave a Reply