- December 20, 2023
- Posted by: Tigist desalgn
- Category: ዜና
ኢምባኮ ህዳር 26/2016 ዓ.ም
የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ተግባራዊ እያደረገ ባለው የManagement Information System (MIS) ፕሮጀክት ካሉት ሰነዶች/Modules/መካከል የቋሚ ንብረት ምዝገባ እና የሰው ሃብት ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ስርዓት ህዳር 26 ቀን 2016 ዓ.ም ስራ አስጀመረ፡፡
በኮርፖሬሽኑ የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ እና ሰነድ መምሪያ ኃላፊ አቶ ዮሃንስ ተስፋዬ እንደገለፁት በኮርፖሬሽኑ ያሉ ንብረቶችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ አደራጅቶ ለማስቀመጥ ምን ያህል ቋሚ ንብረት እንዳለ ለማወቅ፤ የምዝገባ ድግግሞሽን ለማስቀረት፤ በእርጅና ምክንያት ተቀናሽ የሆኑትን ለመለየት እና የኮርፖሬሽኑ ሰራተኛ ከቅጥር ጀምሮ እስከ ጡረታ ድረስ ያለውን እያንዳንዱን ዝርዝር የሰው ሃይል መረጃን አደራጅቶ ለመያዝ የሚያስችል ስርዓት መሆኑን ይህም የኮርፖሬሽኑን አሰራር የሚያዘምንና ፈጣን እንዲሆን የሚያግዝ ነው ብለዋል፡፡
በፕሮጀክቱ ቅድሚያ የተሰጠው የፋይናንስ ሞጁል ከወራት በፊት ተግባራዊ ሆኖ ስራ ላይ የዋለ ሲሆን ከፋይናንስ ቀጥሎ የሰው ኃብት መረጃ አያያዝና የቋሚ ንብረት ምዝገባ በሂደት ተግባራዊ የተደረጉ ሲሆን በቀጣይም የበጀት ስርዓት ፣ ኢንቨንተሪ ፣ፕሮኪውርመንት ሴልስ እና ፕሮጀክት ማኔጅመንት ሞጁሎች ተግባራዊ እንደሚደረጉ ተገልጿል፡፡