Ethiopian Railways Corporation

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 24/2016(ኢዜአ)፦ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር እና ተጠሪ ተቋማቱ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በመሬት መንሸራተት አደጋ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ድጋፍ አደረጉ።

የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም(ዶ/ር)፤ በተቋማቱ በድምሩ የተደረገውን የ10 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተረክበዋል።

በደረሰው አደጋ ተጎጂዎችን ለመደገፍና በዘላቂነት ለማቋቋም የተቀናጁ ተግባራት እየተከናወኑ ነው ብለዋል።

ለመልሶ ማቋቋምና አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ እየተደረገ ያለው ርብርብም ተጠናክሮ መቀጠሉን ኮሚሽነር ሽፈራው ገልጸዋል።

በዛሬው ዕለትም በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር እና ተጠሪ ተቋማቱ ለተደረገው ድጋፍ አመስግነዋል።

በክረምቱ መደበኛና ከመደበኛ በላይ ዝናብ በሚኖርባቸው አካባቢዎች አደጋ እንዳይከሰት ጥንቃቄ እንዲደረግ አስገንዝበው ሊደርስ ከሚችል አደጋ አስቀድሞ ለመከላከል ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ሀብታሙ ሃይለሚካኤል፤ በአደጋው ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች በተቋማቱ በዛሬው እለት ድጋፍ መደረጉን ጠቅሰዋል።

በቀጣይም መልሶ ለማቋቋም በሚደረገው ርብርብ ድጋፋችን ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ አረጋግጠዋል።

ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፤
ድረ  ገፃችንንም ይጎብኙ:  www.erc.gov.et

 

 

 

 

 

 



Leave a Reply