Ethiopian Railways Corporation

ቋንቋ

( ኢምባኮ፡ ሐምሌ 19 ቀን 2016 ዓ.ም)
በኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የሥራ ኃላፊዎች በመንግስት እና የግል አጋርነት የልማት ፕሮጀክት ጥናት እና ትግበራ ላይ በኬንያ ናይሮቢ እ.ኤ.አ ከሐምሌ15-20/2024 ዓ.ም ስልጠና ላይ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

ስልጠናው ሁሉም ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትን በመንግስት ብቻ መስራት መንግስት ላይ የፋይናንስ ጫናዎችን ስለሚፈጥር በመንግስት በተመረጡ ዘርፎች ላይ Public Private Partnership (PPP) የመንግስት እና የግል አጋርነት (የመግአ) ፖሊሲን እና የህግ ማዕቀፎችን መሠረት አድርጎ አቅም እና ልምድ ያላቸው የግል ባለሀብቶችን በማሳተፍ፤ የግል ዘርፉን ሀብት፣ ቴክኖሎጂ፣ የአሰራር ልምድ እና እውቀት በመጠቀም አዳዲስ መሠረተ ልማቶችን ማልማት እና የነበሩትንም ውጤታማ በሆነ መልኩ ተፈላጊውን አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግን ያለመ መሆኑን በስልጠናው ተሳታፊ የሆኑት በኮርፖሬሽኑ የኮርፖሬት ህግ አገልግሎት ቺፍ ኦፊሰር አቶ ካሳሁን ሙላቱ ገልፀዋል፡፡

በርካታ ሀገሮች ብዙ መሠረተ ልማቶችን በመንግስት እና የግል አጋርነት አሰራር ስርአት ተግብረው የጤና እና የትምህርት ተቋማትን፤የመንገድ፣የባቡር መሰረተ ልማት ግንባታ እና ትራንስፖርትን፣የሀይል አቅርቦትን እና ወደቦችን በጋራ በመገንባት እና ለአገልግሎት በማዋል በሀገራቸው ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እድገት ላይ ከፍተኛ ድርሻ እያበረከቱ ይገኛሉ፡፡

ይህ አሰራር በሀገራችን እየተተገበረ መሆኑንና ኮርፖሬሽናችንም በተመረጡ ፕሮጀክቶች ላይ ህጋዊ አካሄዶችን ተከትሎ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችለውን ተግባራት እያከናወነ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ካሳሁን ለዚህም ከአፍሪካ ልማት ባንክ በገንዘብ ሚኒስቴር በኩል በተደረገ የገንዘብ ድጋፍ በኬንያ ናይሮቢ ከተማ እ.ኤ.አ ሐምሌ15-20/2024 ዓ.ም በEastern & Southern African Management Institute /ESAMI/ በተዘጋጀው ስልጠና ላይ የኮርፖሬሽኑ ተወካዮች መሳተፋቸውን አስታውቀዋል፡፡

ስልጠናው በሶስት ምዕራፎች የተከፋፈለ ሲሆን ከዚሀ በፊት በተመሳሳይ ሁኔታ በኬኒያ-ናይሮቢ ከተማ ለአንድ ወር በሁለት ዙር በተሰጠ ስልጠና ሁለቱ የስልጠናው ምዕራፎች ተከናውነዋል፡፡ በዋናነትም የመንግሰት እና የግል አጋርነት (የመግአ) ፕሮጀክት ምንነት እና ጠቀሜታዎቻቸው፣ የመግአ ፕሮጀክቶችን ከመለየት እስከ መተግበር ድረስ ላሉ ተግባራት የሚያስፈልጉ ፖሊሲዎችን እና የህግ ማዕቀፎች ላይ ያተኮረ ነው፡፡
የሶስተኛው ዙር ስልጠናም የመግአ ፕሮጀክቶችን መለየት ስለሚቻልበት አግባብ፣ ለተለዩ የመግአ ፕሮጀክቶች የአዋጭነት ጥናት ማከናወን ሰለሚቻልበት አግባብ፣ የRFQ እና የRFP እንዲሁም የጨረታ ሰነድ ዝግጅት ስራዎችን ለማዘጋጀት የሚያስችሉ ስልጠናዎችን ያካተቱ ናቸው፡፡
ከዚህም በተጨማሪ በዚህ ስልጠና የመግአ ፕሮጀክቶችን ውጤታማ በሆነ አግባብ ለመተግበር የሚችሉ የግል ባለሀብቶችን መምረጥ የሚቻልበት የቴክኒክ ብቃት እና የፋይናንስ አቅም መለኪያዎች ላይ፣ የግል ባለሀብቱ እና መንግስት እያንዳንዳቸው ሰለሚኖራቸው ኃላፊነት እና መብቶች እንዲሁም የመግአ ፕሮጀክቶች በዋናነት የህብረተሰብ ተጠቃሚትን የሚያረጋግጡ እንዲሆኑ ተደርገው ውለታ የሚገባባቸው መሆናቸውን ማረጋገጥ የስልጠናው ዋና ዋናዎቹ ርዕሶች መሆናቸውን አቶ ካሳሁን ገልጸዋል፡፡
በስልጠናው በተለያዩ ወቅቶች አራት የኮርፖሬሽኑ ባለሙያዎች የሰለጠኑ ሲሆን በመግአ ማዕቀፍ ፕሮጀክቶችን ቀርፀው እንዲገቡ የተመረጡ የፌደራል ተቋማት ማለትም የኢፌዴሪ ገንዘብ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ መብራት ኃይል፣የኢትዮጵያ መንገድ አስተዳደር፣ የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን እንዲሁም የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ባለሙያዎች በስልጠናው ላይ ተሳትፈዋል፡፡

ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፤
ድረ  ገፃችንንም ይጎብኙ:  www.erc.gov.et

 

 

 

 

 

 



Leave a Reply