Ethiopian Railways Corporation

ቋንቋ

የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ወደፊት ለመሥራት ላቀዳቸው የመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት ዘርፍ አገልግሎቶች ሥራ የሚያግዝ ከኢትዮጵያ ጭነት አስተላላፊዎች እና የመርከብ ወኪሎች ማህበር Ethiopian Freight Forwarders and Shipping Agents Association (EFFSAA) ጋር የሥልጠና ውል ስምምነት ተፈራረመ።

ስምምነቱን የተፈራረሙት የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የቢዝነስ ዴቨሎኘመንትና ስትራተጂ ዘርፍ ም/ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጌቱ ግዛው (ኢ/ር) እና የኢትዮጵያ ጭነት አስተላላፊዎች እና የመርከብ ወኪሎች ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ብርቱካን ሀረገወይን ናቸው፡፡

በፊርማው ስነ ሥርዓት ወቅት ለሥልጠናው ተግባራዊነት በጋራ እንደሚሠሩ እና በሁለቱ ተቋማት መካከል የተፈረመው ስምምነት በዘርፉ የሚታዩ የአቅም ውስንነቶችን በመቅረፍ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችል የኮርፖሬሽኑ የቢዝነስ ዴቨሎኘመንትና ስትራተጂ ዘርፍ ም/ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጌቱ ግዛው (ኢ/ር) ገልጸዋል፡፡

ወ/ሮ ብርቱካን ሀረገወይን የኢትዮጵያ ጭነት አስተላላፊዎች እና የመርከብ ወኪሎች ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ እንደገለጹት ተቋሙ በአለምቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለው የስልጠና ማእከል መሆኑን ጠቅሰው ከኮርፖሬሽኑ ጋር በቀጣይ በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡

ከአፍሪካ ልማት ባንክ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር በሰጠው እድል በተለያዩ የሙያ ዘርፎች የተሰማሩ አስር ሰራተኞች ሥልጠናውን እየተከታተሉ መሆኑ ታውቋል፡፡

ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፤
ድረ  ገፃችንንም ይጎብኙ:  www.erc.gov.et

 

 

 

 

 

 



Leave a Reply