Ethiopian Railways Corporation

የአዋሽ ነዳጅ ዴፖን ከጅቡቲው ሆራይዘን ተርሚናል ጋር በባቡር የሚያገናኘው ግንባታ በ2017 ዓ.ም እንደሚጀመር ተገለጸ።

የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሺዴ በጅቡቲ ኢነርጂ ሚኒስትር ከተመራ ልዑክ ጋር ተወያይተዋል። የባቡር መስመር ግንባታው ተርሚናሉ ለኢትዮጵያ የሚሰጠውን የነዳጅ መጫን አገልግሎት እንደሚያጠናክር ተገልጿል።

አቶ አሕመድ ሺዴ በጅቡቲ የኢነርጂ ሚኒስትር ዮኒስ አሊ ጉዌዲ ከተመራ የልዑካን ቡድን ጋር በአዲስ አበባ ተወያይተዋል። ውይይቱ የጅቡቲው ሆራይዘን ተርሚናል ለኢትዮጵያ ነዳጅ የመጫን ስርጭት አገልግሎትን በሚያጠናክርበት ጉዳይ ላይ መሆኑን ከገንዘብ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

በተያያዘም የአዋሽ የነዳጅ ዴፖን ከሆራይዘን ተርሚናል ጋር በባቡር የሚያገናኘውን ግንባታ ተፈጻሚ የሚያደርግ ስምምነት መፈራረም በሚቻልበት ሁኔታ ላይም ውይይት ተደርጓል።

በዚሁ መሰረት በሁለቱ አገራት በተሰየሙ የቴክኒክ ኮሚቴዎች ጉዳዩን በማየት ውሉ በመስከረም 2017 ዓ.ም ተፈርሞ ግንባታው እንዲጀመር ከስምምነት ላይ ተደርሷል።

በውይይቱ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማክሮ ኢኮኖሚ አማካሪ አምባሳደር ግርማ ብሩ፣የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ብሩክ ታዬ፣ የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅትና የሆራይዘን ተርሚናል የስራ ኃላፊዎች መገኘታቸው ታውቋል።

ምንጭ፡ ኢዜአ

ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፤
ድረ  ገፃችንንም ይጎብኙ:  www.erc.gov.et

 

 

 

 

 

 



Leave a Reply