Ethiopian Railways Corporation

ቋንቋ

የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን በመንገድ በህንጻ፣በድልድይና በሃይዌይ ግንባታ እንዲሁም በዲዛይንና በማማከር ሥራዎችን ለመሥራት ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን የደረጃ አንድ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭና የአማካሪነት ፈቃድ መውሰዱ ይታወሳል፡፡

ኮርፖሬሽኑ የሮቤ – ጋሴራ – ጊኒር ነባር የጠጠር መንገድ ጥገና ፕሮጀክት ለመስራት ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የ249 ሚሊየን ብር ውል ተፈራርሞ ሥራውን ጀምሯል፡፡ ኮርፖሬሽኑ በራስ ኃይል ገቢ ለማመንጨት ለሚያከናውነው ሥራ ባቋቋመው የኮንስትራክሽን ቢዝነስ ዩኒት አማካኝነት ሥራው እየተካሄደ ይገኛል፡፡
60 ኪ.ሜ የሚሸፍነው የሮቤ – ጋሴራ – ጊኒር ነባር የጠጠር መንገድ ጥገና ኘሮጀክት በምስራቅ ባሌ ዞን በኦሮሚያ ክልል ጋሴራ – ደሎ ሰብሮ – ቀበና – ጊኒርን ጨምሮ በርካታ መንደሮችን እና ከተሞችን የሚያገናኝ ነው፡፡

የኮርፖሬሽኑ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በተካሄደው ምልከታ ገለጻ ያደረጉት የኘሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ተወካይ አቶ ሀብታሙ ቶሎሳ የመንገድ ፕሮጀክቱ 8.9 በመቶ የተጠናቀቀ ሲሆን ከዚህም ውስጥ ማቴሪያል የማምረት ሥራ 21,340m3 ፣ የቦይ ጠረጋ ሥራ 16.64 ኪ.ሜ እና ጠጠር የማልበስ ሥራ 7.2 ኪ.ሜ የተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በምልከታው ወቅት በግንባታው አፈጻጸም እና ባጋጠሙ ችግሮች ዙሪያ ከሠራተኞች ጋር ውይይት ተካሄዷል፡፡ በውይይቱ ወቅት የኮርፖሬሽኑ የቢዝነስ ዴቨሎኘመንት ዘርፍ ም/ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጌቱ ግዛው (ኢ/ር) እና የሰው ሀብት ዘርፍ ም/ዋና ሥራ አስፈጻሚ ውብሸት ሲሳይ (ዶ/ር) የኘሮጀክቱ አፈጻጸም በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑን ገልጸው የተጠቀሱት ችግሮችን ለመፍታት በቀጣይ ከሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች ጋር በጋራ ውይይት የሚካሄድ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የሮቤ – ጋሴራ – ጊኒር ነባር የጠጠር መንገድ ጥገና ፕሮጀክትን የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ግንባታውን እያከናወነ ሲሆን IDCON INFRASTRACTURE DEVELOPMENT CONSULTANT PLC ደግሞ የማማከርና የቁጥጥር ሥራውን እየሠራ ነው፡

ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፤
ድረ  ገፃችንንም ይጎብኙ:  www.erc.gov.et

 

 

 

 

 

 

 



Leave a Reply