Ethiopian Railways Corporation

ቋንቋ

የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ከቻይና (Zhengzhou vocational and technical college) የባቡር ቴክኒክና ሙያ ኮሊጅ ተወካይ ልዑካን ቡድን ጋር ውይይት አካሄደ፡፡

የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ባቡር ኢንስቲቲዩት ከቻይና Zhengzhou vocational and technical college ጋር ስልጠናዎች ለመስጠት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ነሀሴ 10 ቀን 2016 ዓ.ም በኮርፖሬሽኑ የስብሰባ አዳራሽ የኮሌጁ ተወካይ ልዑካን ቡድን በተገኘበት ውይይት ተካሄደ፡፡

ኮርፖሬሽኑን ወክለው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት እና የመግቢያ ንግግር ያደረጉት የኮርፖሬሽኑ ባቡር ኢንሲቲትዩት ቺፍ ኦፊሰር አቶ በቀለ አጦ ውይይቱ ወደፊት በባቡር ዘርፉ ትምህርትና ስልጠና ዙሪያ አብረን ለምንሰራቸው ስራዎች ጉልህ ምዕራፍ የምናስቀምጥበት ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡

በውይይቱ ላይ የኮርፖሬሽኑ ባቡር ኢንስቲትዩት ትምህርትና ስልጠና መምሪያ ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ሲሳይ ጉታ ባቡር ኢንስቲተዩቱ በስልጠና ዘርፉ ያከናወናቸውን ተግባራትና ወደፊትም ከኮሌጁ ጋር ሊሰራቸው ያቀዳቸውን ጉዳዮች በተመለከተ ገለፃ አቅርበዋል፡፡

በተጨማሪም ኢንስቲቲዩቱ ፈቃድ ያለው የስልጠና ማዕከል ሆኖ ስልጠናዎችን ለመስጠት ማሟላት ያለበት መስፈርቶችን በማሟላት ከሚመለከተው አካል ፈቃድ ለማግኘት አስፈላጊውን ሂደት እያከናወነ መሆኑ በውይይቱ ላይ የተገለፀ ሲሆን በቀጣይ ከኮሌጁና በኢንስቲትዩቱ አጋርነት የሚሰጡ ስልጠናዎች በተግባር የታገዙ እንዲሆኑ ለልዑካን ቡድኑ ሃሳብ ቀርቧል፡፡

ልዑካን ቡድኑ በበኩሉ ኮሌጁ በአለምአቀፍ ደረጃ ከበርካታ ሃገራት ጋር በጋራ ያከናወናቸው ተግባራትና በዘርፉ ያለውን እውቅና በተመለከተ ሰፋ ያለ ገለፃ ያቀረበ ሲሆን ከኮርፖሬሽኑ ጋር በቀጣይ በሚኖረው አጋርነት በኢንስቲትዩቱ የተጠየቁ መስፈርቶችን ለማሟላት በሚያደርገው ሂደት ኮሌጁ አስፈላጊውን ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን ተጠቅሷል፡፡

ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፤
ድረ  ገፃችንንም ይጎብኙ:  www.erc.gov.et

 

 

 

 

 

 



Leave a Reply