በኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን እና በጣሊያን COIPA Capital OÜ መካከል የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ

ታኀሣሥ 3/2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን እና በጣሊያን COIPA ካፒታል መካከል የመሠረተ ልማት ኘሮጀክቶች እድገትና ትስስር ለማጠናከር እንዲረዳ በጋራ ለመሥራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡ ስምምነቱን የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የቢዝነስ ዴቨሎኘመንት ስትራተጂ ዘርፍ ም/ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጌቱ ግዛው (ኢ/ር) እና የCOIPA ካፒታል ዋና ስራ አስፈፃሚ Vito Favorito Sciammarella (ዶ/ር) ተፈራርመዋል፡፡ ስምምነቱ የባቡር መስመርና […]
የአዋሽ–ወልዲያ–ሃራ ገበያ የባቡር መስመር በሚያልፍባቸው የአፋር ክልል አካባቢዎች ላይ ከኮርፖሬሽኑ ጋር በቅንጅት እንደሚሠራ ተገለጸ

ኀዳር 24/2017 ዓ.ም (ኢምባኮ) የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር ሀጂ አወል አርባ፣የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ህሊና በላቸው (ኢ/ር)፣ የሥራ አመራር ቦርድ አባል ክቡር አምባሳደር ደግፌ ቡላ ፣ የኢትዮ ጅቡቲ ባቡር አክሲዮን ማኀበር ዋና ስራ አስፈጻሚ ታከለ ኡማ (ኢ/ር) እና የኮርፖሬሽኑ የማኔጅመንት አባላት በተገኙበት እየተገነባ ያለው የአዋሽ ነዳጅ ዴፖ ኘሮጀክት ጉብኝት ተካሂዷል፡፡ በጉብኝቱ ወቅት ኘሮጀክቱ በተሽከርካሪ […]