Ethiopian Railways Corporation

የካቲት 14/2017 ዓ.ም (ኢምባኮ)

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ከፍተኛ አመራሮች የኮርፖሬሽኑን የ2017 በጀት ዓመት የስድስት ወራት የእቅድ አፈጻጸም የካቲት 14/ 2017 ዓ.ም በኮርፖሬሽኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተገኝተው ግምገማ አካሂደዋል፡፡

ግምገማው የተከናወኑ ስራዎች፣ የቀጣይ ወራት የትኩረት አቅጣጫ እና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች ላይ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው፡፡

በስድስት ወር የአፈጻጸም ግምገማ ወቅት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የሥራ ኃላፊዎችና የኮርፖሬሽኑ ማኔጅመንት ተገኝተዋል፡፡

ግምገማው ባለፉት ስድስት ወራት በኮርፖሬት ገቨርናንስና ፋይናንስ፣በፕሮጀክት እና በሪፎርም አፈጻጸም የተከናወኑ ተግባራት እንዲሁም የቀጣይ ትኩረት ጉዳዮች በስፋት ውይይት የተደረጉበት ነው፡፡

ከመንገድ ግንባታና ከተለያዩ የቢዝነስ ሥራዎች 190.4 ሚሊዮን ብር ገቢ ማስመዝገቡ፣የተለያዩ የአሠራር መመሪያዎች ሰነድ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ፣ አዳዲስ ኘሮጀክቶች ወደ ሥራ ለማስገባት በሒደት ላይ መሆኑ እና ከወጪ ቅነሳ አንጻር በግማሽ በጀት ዓመት ውስጥ ኮርፖሬሽኑ ያከናወናቸው ሥራዎች በመልካም ጎን ከታዩ አፈጻጸሞች መካከል የሚጠቀሱ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

በውይይቱ ወቅት የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ህሊና በላቸው (ኢ/ር) ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

በማጠቃለያውም ኮርፖሬሽኑ በ2017 በጀት ዓመት የሰድስት ወራት የእቅድ አፈጻጸም እንዲሁም የተከናወኑ ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ፣ የፋይናንስ ተግዳሮቶችን ለማሻሻል ከሚመለከታቸው መንግሥታዊ ተቋማት ጋር መስራት እንደሚያስፈልግ፣ የውስጥ ኦዲትን በተመለከተ ይበልጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥል፣ የታቀዱ የቢዝነስ ሥራዎች ወደ ተግባር እንዲገቡ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ኃላፊዎች አስተያየት ተሰጥቷል፡፡

 

 

 

ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፤
ድረ  ገፃችንንም ይጎብኙ:  www.erc.gov.et

 

 

 

 

 

 

 



Leave a Reply