Ethiopian Railways Corporation

የካቲት 25 ቀን 2017 (ኢምባኮ)
በኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን እና በKorea Railroad Corporation (KORAIL) መካከል በባቡር ኢንዱስትሪ ዘርፍ አብሮ በትብብር ለመሰራት የሚያስችል የሁለትዮሽ የመግባቢያ የፊርማ ስምምነት ሥነ-ስርዓት የካቲት 25 ቀን 2017 ዓ.ም በሂልተን ሆቴል ተካሄደ፡፡
የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ህሊና በላቸው (ኢ/ር) በወቅቱ እንደተናገሩት የባቡር መሠረተ ልማት ግንባታ; የጥገና፣ የማማከር እና የቴክኒክ ስልጠና በመግባቢያ ሰነዱ ላይ የተገለጹ በተቋማቱ መካከል የሚኖሩ የትብብር መስኮች መሆናቸውን እና ስምምነቱ በሀገራችን የተጀመረውን የባቡር ኢንዱስትሪ ለማስፋፋት የተያዘውን እቅድ እውን ለማድረግ ከፍተኛ ድርሻ እንደሚኖረው ገልጸዋል፡፡
የKorea Railroad Corporation ዋና ስራ አስፈፃሚ Mr. Han Moon hee በበኩላቸው የኢትዮጵያና ኮሪያ ግንኙነት የቆየ ታሪክ እንዳለው ጠቅሰው በባቡር ዘርፉ በሀገራችን ለመሰማራት ትልቅ ፍላጎት እንዳላቸው አስታውቀዋል፡፡ የኮሪያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን በዘርፉ ብዙ ልምድ ያካበተ እና በተለያዩ አፍሪካ ሀገራት በባቡር ዘርፍ ላይ እየተሳተፈ መሆኑን የገለጹት ዋና ሥራ አስፈጻሚው በትብብር ስምምነቱ መሰረት በቀጣይ ያላቸውን ልምድ እና አቅም ከኮርፖሬሽኑ ጋር አብረው ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
በማጠቃለያውም የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር አገልግሎትን ተዘዋውረው ጐብኝተዋል፡፡

ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፤
ድረ  ገፃችንንም ይጎብኙ:  www.erc.gov.et

 

 

 

 

 

 

 



Leave a Reply