Ethiopian Railways Corporation

በአንድ ጀምበር 500 ሚሊዮን ችግኝ የመትከል መርሃ-ግብር ተካሄደ

ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ/ም (ኢምባኮ) የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ማኔጅመንትና እና ሰራተኞች በጋራ በመሆን በአንድ ጀምበር የ500 ሚሊዮን የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብርን በተመለከተ ሐምሌ 10 2015 ዓ.ም ዕለት በዋናው መሥሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ አሻራቸውን አኑረዋል፡፡ ሀገር አቀፍ የችግኝ ተከላ የንቅናቄ መርሃ ግብር ‹‹ነገን ዛሬ እንትከል!›› በሚል መሪ ቃል ተግባረዊ ሲሆን ኮርፖሬሽኑ የዚሁ ፕሮግራም አንድ […]

የManagement Information System (MIS) ስልጠና ለኮርፖሬሽኑ ባለሙያዎች የካቲት 22 ቀን 2015 ዓ.ም በኮርፖሬሽኑ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የስልጠና ማዕከል ተጀመረ፡፡

የስልጠናውን መጀመር አስመልክተው የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ተወካይ  ጌቱ ግዛው(ኢ/ር) ባደረጉት ንግግር  የስልጠናው ዋና አላማ የኮርፖሬሽኑን አሰራር ዘመናዊ በማድረግ ከወረቀት ነፃ የሆነ ፈጣን የመረጃ አያያዝ እና ልውውጥ ስርዓትን ለማስፈን መሆኑን ገልፀው ሰልጣኞች ለስልጠናው ትኩረት ሰጥተው መከታተል እንዳለባቸው እና ከሰለጠኑ በኋላ በየስራ ክፍላቸው ያሉ ባለሙያዎችን በማሰልጠን ወደ ትግበራ ስርአት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ በኮርፖሬሽኑ የአይ.ሲቲ እና ሰነድ መምሪያ […]

የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢ/ር ህሊና በላቸው በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር ሬሚ ማርቹክስ ጋር ተወያዩ፡፡

ውይይቱ ሁለቱ ሀገራት አብሮ ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት መሠረት ያደረገ ሲሆን የፈረንሳይ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በባቡር መሠረተ ልማት፤በባቡር ትራንስፖርት እንዲሁም በሎጂስቲክስ እና መልቲ ሞዳል ስራዎች ላይ መሰማራት በሚችሉበት ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡ በመልቲ ሞዳል ስራዎች ላይ የተሰማሩ የፈረንሳይ ተቋማት በኢትዮጵያ ሊሳተፉ በሚችሉበት ሁኔታ፤በሀገራችን በቀጣይ ሊገነቡ በእቅድ በተያዙ የባቡር መሠረተ ልማቶች መንግስት ባስቀመጣቸው አማራጮች ላይ፤በተለያዩ የፋይናንስ አማራጮች ከተለያዩ የኢትዮጵያ […]