Ethiopian Railways Corporation

ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ/ም (ኢምባኮ)
የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ማኔጅመንትና እና ሰራተኞች በጋራ በመሆን በአንድ ጀምበር የ500 ሚሊዮን የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብርን በተመለከተ ሐምሌ 10 2015 ዓ.ም ዕለት በዋናው መሥሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ አሻራቸውን አኑረዋል፡፡

ሀገር አቀፍ የችግኝ ተከላ የንቅናቄ መርሃ ግብር ‹‹ነገን ዛሬ እንትከል!›› በሚል መሪ ቃል ተግባረዊ ሲሆን ኮርፖሬሽኑ የዚሁ ፕሮግራም አንድ አካል እንደመሆኑ መጠን የአረንጓዴ አሻራን በተግባር ማሳየት ችሏል፡፡

በችግኝ ተከላው ወቅት የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ ህሊና በላቸው ( ኢ/ር ) “ሀገራችን የያዘችውን የአረንጓዴ አሻራ የማኖር እቅድን ተግባራዊ በማድረግ ከብክለት ነፃ የሆነ የአከባቢ አየር ለመፍጠር የበኩላችን አስተዋፅኦ የምናበረክት ሲሆን የባቡር ኢንዱስትሪው ለዚህ መርህ አንዱ ተጠቃሽ በመሆኑ የሀገራችንን ራዕይ ለማሳካት የበኩላችንን ድርሻ እንወጣለን” ብለዋል፡፡ አያይዘውም ዛሬ የሚተከለው ችግኝ ለነገ ተተኪ ትውልድ የሚጠቅምና ትልቅ ተስፋ የሚደረግበት በመሆኑ ችግኞችን ከመትከል ባለፈ መጽደቃቸውን በቅርበት ሆነን እንከታተላለን ብለዋል፡፡

ኮርፖሬሽኑ ከዚህ ቀደም በኦሮሚያ ብራሄዊ ክልላዊ መንግስት ምስራቅ ሸዋ ዞን ሉሜ ወረዳ ችግኞችን በመትከልና በመንከባከብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጉ ይታወቃል፡፡ በቀጣይም የባቡር መሠረተ-ልማቶች በሚገኙባቸው አካባቢዎች መርሐ-ግብሩ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡



Leave a Reply