Ethiopian Railways Corporation

ኢምባኮ ሚያዝያ 12/2018 .

የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን“ኢትዮጵያ ትገነባለች፤ ፈጠራ፣ ፍጥነትና ጥራት ለመሠረተ ልማት እመርታ” በሚል መሪ ቃል በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል እየተካሄደ ባለው የመሠረተ ልማትና ኮንስትራክሽን ሳምንት ላይ በተዘጋጀው የፓናል ውይይት ላይ ተሳታ ሆኗል፡፡

ትስስር፣መሠረተ ልማት፣ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ  በሚል ርዕስ  የተዘጋጀው የፓናል ውይይት የመሩት የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ደንጌ ቦሩ ሲሆኑ፣የመሠረተ ልማት ዝርጋታ ለሀገራዊ እና ቀጠናዊ ትስስርን መፍጠር፤ ጊዜ፣ወጪ በመቆጠብ ምርትና አገልግሎትን በማንቀሳቀስ ለሀገራችን ሁለንተና ዕድገት ወሳኝ ሚና እንዳለው አብራርተዋል፡፡

ኢ/ር ህሊና በላቸው የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ባቡር መሠረተ ልማት ስትራያዊ ጠቀሚታ፤

ኢ/ር መሐመድ አብዱራህማን ከኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር የመንገድ ልማት ዝርጋታ ዕድገትና የቀጣይ ዕቅድ፤

አቶ መሐመድ አደም ከኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር  የገጠር ትስስር የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ  ፅ/ቤት ኃላፊ የመወያያ ፅሁፎች አቅርበዋል፡፡

በውይይቱ ላይ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢ/ር ህሊና በላቸው “የባቡር መሠረተ ልማት ስትራቴጂያዊ ጠቀሜታ” በሚል ርዕስ ባቀረቡት የመነሻ ጽሑፍ የባቡር ልማት ጊዜንና ወጪን በመቆጠብ፣ በኤሌክትሪክ የሚሰራ ዘመናዊ የባቡር መስመር መዘርጋን አብራርተዋል፡፡

የሀገሪቱን የኢንዱስትሪ ማዕከላት፣ከአጎራባች ወደቦች ጋር በማገናኘት ቀጠናዊ ትትስርን ለመፍጠር ስትራተጂ ነድፎ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ኮርፖሬሽኑ ባቋቋመው የባቡር ኢንስቲትዩት ባለሙያዎችን በራስ አቅም በማሰልጠን ላይ እንደሚገኝ፣ የሎጂስቲክስ ድርጅት በመመስረት መልቲሞዳል አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን በተጨማሪም የተለያዩ ቢዝነስ ዩኒቶችን በማቋቋም የኮንስተራክስሽን ዲዛይን እና ማከር አገልግሎትችን እየሰጠ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ ተወዳዳሪ አገልግሎት ለመስጠት ብሎም ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት ቁልፍ መሠረት መሆኑን አስገንዝበዋል።

በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች በፓናሊስቶቹ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።

 

ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፤

ፌስቡክ፡  https://www.facebook.com/…/Ethiopian-Railways…/
ቴሌግራምhttps://t.me/EthiopianRailwaysCorporati
ድረ  ገፃችንንም ይጎብኙ:  www.erc.gov.et