ኮርፖሬሽኑ የISO 9001፣ ISO 14001 እና ISO 45001 መስፈርቶችን በማቀናጀት ለመተግበር ያለመ የIMS ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በዋና መስሪያ ቤቱ አካሂዷል ።
ስልጠናው በQualitek System Consultancy PLC አማካሪ አቶ የአለም ብርሃን ይታየው የተሰጠ ሲሆን፣ የሂደት አቀራረብ፣ የአደጋና ዕድል አስተዳደር፣ የሰነድ ቁጥጥር፣ KPI እና የማሻሻያ እርምጃዎችን አካቶ እንዲሰጥ ሆኗል ።
የኮርፖሬሽኑ የIMS ፕሮጀክት ተጠሪ አቶ ታደለ ደገፋ በበኩላቸው የስልጠናው ተሳታፊዎች ያገኙትን የIMS ግንዛቤ ወደ ተግባር እንዲቀይሩ ይረዳቸዋል ያሉም ሲሆን፤ ኮርፖሬሽኑ የISO ሰርተፍኬት ለማግኘት የጀመረውን ጉዞ በማጠናከር፣ በተቀናጀ የአስተዳደር ስርዓቱ ዘላቂ ትግበራ ላይ እያንዳንዱ ሠራተኛ የድርሻውን ኃላፊነት እንዲወጣ ያስችለዋልም ብለዋል ።
የስልጠናው ተሳታፊዎችም የIMSን አስፈላጊነት፣ የሂደት አቀራረብንና የአደጋ አስተዳደርን በተግባር ለመተግበር ግልጽ መመሪያ እንዳገኙም ገልጸዋል።
ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፤
ድረ ገፃችንንም ይጎብኙ: www.erc.gov.et
