የመደመር መንግሥት ምስረታ ፤ ኢትዮጵያ የጀመረችውን የልማት፣ የትስስርና የብልጽግና ጉዞ የምታጠናክርበት አዲስ ምዕራፍ ነው።
የመደመር መንግስት ለባቡር ዘርፍ የሰጠውን የላቀ ትኩረት ተከትሎ የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ፣ ከተሞችን፣ የኢኮኖሚ ኮሪደሮችንና አጎራባች ወደቦችን የሚያገናኝ ዘመናዊ፣ ፈጣን፣ለአካባቢ ተስማሚ የባቡር መሠረተ ልማት በመገንባት ብሎም ለዘላቂና ተወዳዳሪ ኢኮኖሚ ግንባታ የሚሆን አስቻይ የባቡር መሠረተ ልማት በመዘርጋት ላይ ይገኛል ።
የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የአዲስ አበባ ቀላል ባቡርንና የኢትዮ–ጂቡቲ የባቡር መስመርን ግንብቶ ለአገልግሎት አብቅቷል፡፡
ኮርፖሬሽኑ ከባቡር መሰረተ ልማት ግንባታ ባሻገር በመልቲ ሞዳል ሎጀስቲክስና በሌሎች ተያያዥ የንግድ ዘርፎች ያለውን ተሳትፎ እያስፋፋ ይገኛል፡፡
ኮርፖሬሽኑ ሁለተናዊ ሀገራዊ ብልጽግና እና አካታች የልማት ስኬት የሚረጋገጠው በሰለጠነ የሰው ኃይል በመታገዝ ጭምር መሆኑን በጽኑ በመረዳት ባቋቋመው የባቡር በአካዳሚ ብቁ የባቡር ባለሙያዎችን በማሰልጠን ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ በቢሾፍቱ ከተማ በምስራቅ አፍሪካ ተወዳዳሪ የባቡር ልህቀት ማዕከል ግንባታን ለመጀመር የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በማከናወን ላይ ነው፡፡
ኮርፖሬሽኑ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ለደንበኞቹ፣ ለአጋር ተቋማትና ለኮርፖሬሽኑ ማህበረሰብ፤ ለመደመር መንግሥት ምስረት እንኳን አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልጻል፡፡
ለዘመነ እድገትና ትስስር፣
የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን!
ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፤