Ethiopian Railways Corporation

ዘመናዊ የባቡር መጓጓዣ ሥርዓት ሰዎችን እና እቃን ከማጓጓዝ ባሻገር ዘርፈ  ብዙ ኃላፊነቶችን በአንድነት መወጣት  ይጠበቅበታል ። የስራ ላይ ደህንነትን ጠብቆ መሥራት፣ አካባቢን መንከባከብና መጠበቅ፣ ደረጃውን የጠበቀ አስተማማኝ አገልግሎት መስጠት፣ እንዲሁም የደንበኞችን፣ የሠራተኞችን፣ የአጋሮችንና የማኅበረሰቡን እምነት በይበልጥ የማጠናከር ኃላፊነት ይኖርበታል ።

የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን (ERC) ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ዕድገትና ለቀጠናዊ  ትስስር የላቀ አስተዋፅዖ የሚያደርግ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ አስተማማኝ፣ ውጤታማና ዘላቂ የባቡር መጓጓዣ ሥርዓት በመገንባት በላቀ ኃላፊነት ለማስተዳደር ያለውን ቁርጠኝነት ልክ እንደ ጥንቱ ሁሉ ዛሬም   በስራዎቹ  ሁሉ በማረጋገጥ ላይ ይገኛል።

ይህ የተቀናጀ የአስተዳደር ሥርዓት (framework) በሚከተሉት ዓለም አቀፍ የደረጃ መስፈርቶች ላይ የተመሠረተም ነው፦

• ISO 9001:2015 —ግዜውን የዋጀ ተመጣጣኝ ጥራትንና የደንበኞችን እርካታ ማረጋገጥ ላይ የሚያተኩር።
• ISO 14001:2015 — ሥርዓታዊ የአካባቢ አስተዳደርን የሚደግፍ።
• ISO 45001:2018 — የተሻለ የሥራ ቦታ ደህንነትንና ጤናማ የስራ አካባቢን የሚመለከት።
ይሕ ተቋማዊ የተቀናጀ የአስተዳደር ሥርዓት (  policy) በአምስት ዋና ዋና የቅድሚያ ቅድሚያ ተግባራት ላይ የሚያተኩር ይሆናል ፦

• አሁናዊ ደረጃዎችን የጠበቀ ጥራት ያለው የባቡር መሠረተ ልማትና የኮርፖሬሽን አገልግሎቶችን ማቅረብ፤
• ሠራተኞችን፣ ተቋራጮችን፣ ጎብኚዎችንና ሌሎች ባለ ድርሻ  አካላትን ከሥራ አካባቢ አደጋዎች በላቀ ዝግጁነትና ኃላፊነት መጠበቅ ፤
• ብክለትን መከላከልና ሀብትን በብቃት መጠቀምን   ማበረታታት፤
• አደጋንና ዕድልን መሠረት ያደረገ አስተሳሰብን በዕቅድና በአሠራር ውስጥ ማካተት፤
• ተጠያቂነትን፣ ብቃትን፣ የባለድርሻ አካላትን እምነትና ቀጣይነት ያለውን የማሻሻያ ስርዓት ማጠናከር።

ይህ ፖሊሲ  በኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን  (ERC )እና  በቁጥጥሩ ሥር ባሉ ተቋማት ውስጥ በሚሠሩ ሁሉም ሠራተኞች እና ባለ ድርሻ አካላት በጥብቅ ዲስፒሊን ተፈጻሚ የሚደረግ ይሆናል ። በኮርፖሬሽኑ መዋቅር በየደረጃው ያለ የስራ አመራር የፖሊሲውን ተግባራዊነት የማረጋገጥ ኃላፊነት የሚኖርበት ሲሆን፣በተመሳሳይ እያንዳንዱ ሠራተኛ የተቀናጀ የአስተዳደር  (management )  ሥርዓቱን ውጤታማነትና ቀጣይነት ያለው መሻሻልን ለማረጋገጥ የድርሻውን አስተዋፅዖ  ማበርከት ይጠበቅበታል።

ይህ ቁርጠኝነት የERCን ራዕይ፣ “የኢትዮጵያን ቀጣይነት ያለው የዕድገት የእንቅስቃሴ፣ የንግድና የለውጥ ኃይል መሆንን”በተጨባጭ ያጠናክራል።
ኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት!

ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፤

ፌስቡክ፡  https://www.facebook.com/…/Ethiopian-Railways…/
ቴሌግራም:  https://t.me/EthiopianRailwaysCorporati
ድረ  ገፃችንንም ይጎብኙ:  www.erc.gov.et