ጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም
በአስፈላጊ የትብብር መስኮች በአጋርነት ለመስራት የሚያስችለውን የሁለትዮሽ ስምምነት የፈረሙት የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢ/ር ህሊና በላቸው እና የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ሸጋው ሙሉጌታ ናቸው።
በሁለትዮሽ ስምምነቱ ማዕቀፍ ሁለቱም ተቋማት በባቡር መሰረት ልማት ዝርጋታ፤በባቡር አካላት ምርት በሁለቱም ተቋማት ያለን አሁናዊ አቅም አሟጦ ለመጠቀም እና ቀጣይ የአቅም ግንባታ ስራዎችን በጋራ ለማከናወን ተስማምተዋል።
የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ህሊና በላቸው በመርሀ -ግብሩ ላይ እንዳሉት ኮርፖሬሽኑ በተለዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚያካሂዳቸውን የባቡር መሰረተ ልማት ዝርጋታ ስራዎች በሚመለከት ከኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል መልካም አጋጣሚ መፈጠሩ የሁለቱንም ተቋማማት የስራ አፈጻጸም እና ሀገራዊ የልማት አስተዋጽኦ ለማላቅ ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር ነው ያሉት መለዋወጫዎችን በሀገር ውስጥ በቅርበት ለማግኘት እንዲቻል ብሎም የውጭ ምንዛሪን ለማዳን ከግሩፑ ጋር ተቀራርበው በአጋርነት የሚሰሩ ሰለመሆናቸው በአጽንኦት ተናግረዋል፡፡
የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ሸጋው ሙሉጌታ በበኩላቸው በተቋማቸው ውስጥ ያሉ ኢንዱስትሪዎች የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የባቡር መሰረተ ልማት ዝርጋታን ጨምሮ ለሚያከናውናቸው ልዩ ልዩ የልማት ስራዎች ግብአት የሚሆኑ ምርቶች የማምረት የተሟላ አቅም እንዳለው ገልፀው ግሩፑ በዋነኝነት ተኪ ምርቶች ላይ በማተኮር የሚሰራ መሆኑ የኮርፓሬሽኑን በየደረጃው ያሉ የልማት ስራዎች ለመደገፍ ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር ነውም ብለዋል።
በስምምነቱ ወቅት የሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችን ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
ከኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት !
ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፤
