Ethiopian Railways Corporation

በባቡር ዘርፍ ዙሪያ የማሻሻያ ሀሳቦች ላይ ግብአት ለማሰባሰብ ያለመ ጉብኝትና ውይይት ተካሄደ

ታህሳስ 18 ቀን 2016 ዓ.ም (ኢምባኮ ) የገንዘብ ሚኒስቴር የኢኮኖሚ ማሻሻያ እና ፕራይቬታይዜሽን ጽ/ቤት እና የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመር ከታህሳስ 16-17/2016 ዓ.ም የመስክ ጉብኝት አደረጉ፡፡ የጉብኝቱ ዓላማ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ ማሻሻያ ለማድረግ በእቅድ ከያዛቸው ዘርፎች አንዱ የባቡር ዘርፍ በመሆኑ ድጋፍ ለማድረግ የሚያስፈልጉ የፖሊሲ፣አስተዳደራዊ እና አደረጃጀት ላይ የማሻሻያ ሀሳቦችን ለማቅረብ […]

በኮርፖሬሽኑ ቀጣይ የስራ አቅጣጫ ላይ ውይይት ተካሄደ

ህዳር 27/2016ዓ.ም ኢምባኮ የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የስራ ኃላፊዎችና አጠቃላይ ሰራተኞች በኮርፖሬሽኑ ቀጣይ የስራ አቅጣጫ ላይ ህዳር 27/2016 ዓ.ም በኮርፖሬሽኑ የስብሰባ አዳራሽ ውይይት አካሄዱ፡፡ በመድረኩ ላይ ተገኝተው ገለፃ ያደረጉት የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ ህሊና በላቸው (ኢ/ር) ኮርፖሬሽኑ በለውጥ ሂደት ላይ በመሆኑ ሰራተኛው ለሚፈለግበት ለውጥ በመዘጋጀት እራሱን የለውጡ አካል አድርጎ በመስራት ተቋሙ ውጤታማ ሆኖ እንዲቀጥል በመተጋገዝ […]

የቋሚ ንብረት ምዝገባና የሰው ሃብት ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ተግባራዊ ሆነ

ኢምባኮ ህዳር 26/2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ተግባራዊ እያደረገ ባለው የManagement Information System (MIS) ፕሮጀክት ካሉት ሰነዶች/Modules/መካከል የቋሚ ንብረት ምዝገባ እና የሰው ሃብት ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ስርዓት ህዳር 26 ቀን 2016 ዓ.ም ስራ አስጀመረ፡፡ በኮርፖሬሽኑ የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ እና ሰነድ መምሪያ ኃላፊ አቶ ዮሃንስ ተስፋዬ እንደገለፁት በኮርፖሬሽኑ ያሉ ንብረቶችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ አደራጅቶ ለማስቀመጥ ምን […]

በዲዛይን ጥናት ላይ ውይይት ተካሄደ

ኢምባኮ ህዳር 25/03/2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን በዋና መስሪያ ቤቱ ለሚያስገነባው ሁለገብ ማዕከል ህንፃ እየተጠና ባለው ዲዛይን ላይ ከኮርፖሬሽኑ የስራ ኃላፊዎችና የጥናት ቡድን ጋር ህዳር 25 ቀን 2016 ዓም በኮርሬሽኑ የስብሰባ አዳራሽ ውይይት አካሄደ፡፡ ጥናቱ የተዘጋጀው China Rail Transit Engineering Consultancy (CRTEC) በተባለ አማካሪ ድርጅት የተዘጋጀ ሲሆን የዲዛይን፣ የቴክኒክ እና የፋይናንስ ፍላጎት በዝርዝር ቀርቧል፡፡ […]

የኢምባኮ የሥራ አመራር ቦርድ 93ኛ መደበኛ ስብሰባ ተካሄደ

ኀዳር 22 ቀን 2016 ዓ.ም (ኢምባኮ) የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፓሬሽን የሥራ አመራር ቦርድ 93ኛ መደበኛ ስብሰባ ኀዳር 22 ቀን 2016 ዓ.ም በትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ዋና መሥሪያ ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተካሄደ ፡፡ በዛሬው ዕለት የሥራ አመራር ቦርዱ በተለያዩ አጀንዳዎች ዙሪያ ውይይት ካካሄደ በኋላ የኮርፖሬሽኑን ስራ ወደፊት የሚያስኬዱ ስትራተጂካዊ እና ወሳኝ ሚና ያላቸውን ውሳኔዎችን አሳልፏል። ኮርፖሬሽኑ በራስ ሀይል […]

የቋሚ ኮሚቴ አባላት ውይይት አካሄዱ

ኀዳር 17, 2016 ዓ.ም ( ኢምባኮ) በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ በኮርፖሬሽኑ የ2016 ሩብ በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ዙሪያ ከማኔጅመንት አባላት ጋር ኀዳር 17 ቀን 2016 ዓ.ም. በሂልተን ሆቴል ውይይት አካሂዷል በውይይቱ መክፈቻ ወቅት የኮርፖሬሽኑ ም/ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢ/ር ጌቱ ግዛው እንደገለጹት የቋሚ ኮሚቴ አባላቱ የተቋሙን አፈጻጸም ትኩረት ሰጥቶ […]

የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት አስተዳደር ስልጠና ተሰጠ

የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ባቡር አካዳሚ ዘርፍ ከኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት አስተዳደር ስልጠና በግዮን ሆቴል እየተሰጠ ይገኛል፡፡ የስልጠናው ዓላማ ኮርፖሬሽኑ በአሁኑ ወቅት የስትራቴጂ ለውጥ አድርጎ እየጀመራቸው ያሉ ፕሮጀክቶች እና የቢዝነስ ዩኒት ስራዎች ላይ አቅም በማሳደግ በቀጣይ ለሚሰራቸው ፕሮጀክቶች ተወዳዳሪ በመሆን አዲስ እይታ መፍጠር የሚያስችል ግንዘቤ ለማሳደግ መሆኑን የኮርፖሬሽኑ የባቡር አካዳሚ ዘርፍ ትምህርትና […]

የ2016 በጀት የመጀመሪያ ሩብ አመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት

ጥቅምት 30/2ዐ16 ዓ.ም (ኢምባኮ) የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን በ2016 በጀት የመጀመሪያ ሩብ አመት የስራ አፈፃፀም እና የኢንቨስትመንት ስራዎች ሪፖርት ከገንዘብ ሚኒስቴር እና የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታ እና አስተዳደር ከመጡ የስራ ኃላፊዎች ጋር ጥቅምት 29 ቀን 2016 ዓ.ም ውይይት አካሂዷል፡፡ ===========================    

የቋሚ ንብረት ምዝገባ ስልጠና ተጀመረ

  መስከረም 28/2ዐ16 ዓ.ም (ኢምባኮ) በኮርፖሬሽኑ እየተጠና ባለው የManagement Information System (MIS) ፕሮጀክት ውስጥ ካሉት ሰነዶች/Modules/መካከል የቋሚ ንብረት ምዝገባ ስልጠና ለባለሙዎች መስከረም 28 ቀን 2016 ዓ.ም በአይ.ሲ.ቲ. ስልጠና ማእከል ተጀመረ፡፡ በኮርፖሬሽኑ የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ እና ሰነድ መምሪያ ኃላፊ አቶ ዮሃንስ ተስፋዬ ስልጠናው ያስፈለገበት ምክንያት በኮርፖሬሽኑ ያሉ ንብረቶችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ አደራጅቶ ለማስቀመጥ እና ምን ያህል ቋሚ […]

ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ

የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን በዋና መስሪያቤቱ ለሚያስገነባው ሁለገብ ማዕከል (የንግድና የመኖሪያ)ህንፃ የዲዛይን ጥናትን አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር መስከረም 24 ቀን 2016 ዓ.ም በካፒታል ሆቴል ውይይት አካሄደ፡፡ የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ ህሊና በላቸው (ኢ/ር) ባደረጉት የመግቢያ ንግግር ተቋሙ በአዋጅ የተሰጠውን ተልእኮ እውን ለማድረግ ባለው የሰለጠነ የሰው ሀይል የባቡር ፕሮጀክቶችን ገንብቶ ለአገልግሎት በማብቃት በሀገራችን በተለይ በትራንስፖርት እና […]