የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር እና ተጠሪ ተቋማቱ ለጎፋ ዞን አደጋ ተጎጂዎች ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 24/2016(ኢዜአ)፦ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር እና ተጠሪ ተቋማቱ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በመሬት መንሸራተት አደጋ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ድጋፍ አደረጉ። የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም(ዶ/ር)፤ በተቋማቱ በድምሩ የተደረገውን የ10 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተረክበዋል። በደረሰው አደጋ ተጎጂዎችን ለመደገፍና በዘላቂነት ለማቋቋም የተቀናጁ ተግባራት […]
በመንግስት እና የግል አጋርነት የልማት ፕሮጀክት ጥናት እና ትግበራ ላይ ስልጠና ተካሄደ

( ኢምባኮ፡ ሐምሌ 19 ቀን 2016 ዓ.ም) በኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የሥራ ኃላፊዎች በመንግስት እና የግል አጋርነት የልማት ፕሮጀክት ጥናት እና ትግበራ ላይ በኬንያ ናይሮቢ እ.ኤ.አ ከሐምሌ15-20/2024 ዓ.ም ስልጠና ላይ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ ስልጠናው ሁሉም ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትን በመንግስት ብቻ መስራት መንግስት ላይ የፋይናንስ ጫናዎችን ስለሚፈጥር በመንግስት በተመረጡ ዘርፎች ላይ Public Private Partnership […]
ኮርፖሬሽኑ የአቅም ግንባታ ስልጠና ውል ተፈራረመ

የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ወደፊት ለመሥራት ላቀዳቸው የመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት ዘርፍ አገልግሎቶች ሥራ የሚያግዝ ከኢትዮጵያ ጭነት አስተላላፊዎች እና የመርከብ ወኪሎች ማህበር Ethiopian Freight Forwarders and Shipping Agents Association (EFFSAA) ጋር የሥልጠና ውል ስምምነት ተፈራረመ። ስምምነቱን የተፈራረሙት የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የቢዝነስ ዴቨሎኘመንትና ስትራተጂ ዘርፍ ም/ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጌቱ ግዛው (ኢ/ር) እና የኢትዮጵያ ጭነት አስተላላፊዎች እና […]
በኮርፖሬሽኑ በኤም.አይ.ኤስ ሲስተም የሽያጭ ሞጁል ጥናት ተጠናቆ ትግበራ ተጀመረ

ተቋሙ የሚያከናውናቸውን የተለያዩ የገቢ ማስገኛ ስራዎች በዘመናዊ አሰራር እንዲታገዙ ለማድረግ የገቢ እና ወጪ ሥራዎችን በዘመናዊ መልኩ ለመቆጣጠር የሚያስችል፤ጊዜ ቆጣቢ እና የወረቀት ስራዎችን የሚያስቀር የኤም.አይ.ኤስ ሲስተም የሽያጭ ሞጁል የአሠራር ሥርዓት ከስራው ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያላቸው ባለሙያዎችን በማሠልጠን ወደ ሥራ የተገባ መሆኑን አቶ ዮሀንስ ተስፋዬ የኮርፖሬሽኑ የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ ገልፀዋል፡፡ ይህ ስራ በዋናነት የሚከናወነው በቢዝነስ […]
የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም ተካሄደ

ታኀሣሥ 27 ቀን 2016 ዓ.ም፣ (ኢምባኮ) የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ አስር ለሚገኙ አቅመ ደካማ የማህበረሰብ ክፍሎች የገና በዓልን አስመልክቶ ታህሳስ 27 ቀን 2016 ዓ.ም በወረዳው ቅጥር ግቢ በመገኘት የማዕድ ማጋራት መርሐ ግብር አካሄደ፡፡ ኮርፖሬሽኑ ማህበራዊ ኃላፊነትን ከመወጣት አኳያ በተለያዩ ጊዜያት ድጋፍ ለሚሹ አካላት ድጋፍ በማድረግ የበኩሉን አስተዋፅኦ እያበረከተ የሚገኝ ሲሆን በዚህም […]
የኮርፖሬት ገቨርናንስና ፋይናንስ ሥርዓት ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

የመንግሥት የልማት ድርጅት ይዞታ አስተዳደር ለኮርፖሬሽኑ የሥራ አመራር ቦርድ አባላትና ለኮርፖሬሽኑ የማኔጅመንት አባላት በኮርፖሬት ገቨርናንስና ፋይናንስ ስርዓት ላይ ያተኮረ ሥልጠና ታኀሣሥ 25 ቀን 2016 ዓ.ም በሒልተን ሆቴል አካሄደ፡፡ በስልጠናው መክፈቻ ወቅት የመንግሥት የልማት ድርቶች ይዞታና አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ሀ/ሚካኤል እንደገለጹት የልማት ድርጅቶች ውጤታማና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ዘመናዊ የኮርፖሬት አስተዳደር እና የኮርፖሬት ፋይናንስ ሥርዓት መዘርጋትና […]
በባቡር ዘርፍ ዙሪያ የማሻሻያ ሀሳቦች ላይ ግብአት ለማሰባሰብ ያለመ ጉብኝትና ውይይት ተካሄደ

ታህሳስ 18 ቀን 2016 ዓ.ም (ኢምባኮ ) የገንዘብ ሚኒስቴር የኢኮኖሚ ማሻሻያ እና ፕራይቬታይዜሽን ጽ/ቤት እና የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመር ከታህሳስ 16-17/2016 ዓ.ም የመስክ ጉብኝት አደረጉ፡፡ የጉብኝቱ ዓላማ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ ማሻሻያ ለማድረግ በእቅድ ከያዛቸው ዘርፎች አንዱ የባቡር ዘርፍ በመሆኑ ድጋፍ ለማድረግ የሚያስፈልጉ የፖሊሲ፣አስተዳደራዊ እና አደረጃጀት ላይ የማሻሻያ ሀሳቦችን ለማቅረብ […]
በኮርፖሬሽኑ ቀጣይ የስራ አቅጣጫ ላይ ውይይት ተካሄደ

ህዳር 27/2016ዓ.ም ኢምባኮ የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የስራ ኃላፊዎችና አጠቃላይ ሰራተኞች በኮርፖሬሽኑ ቀጣይ የስራ አቅጣጫ ላይ ህዳር 27/2016 ዓ.ም በኮርፖሬሽኑ የስብሰባ አዳራሽ ውይይት አካሄዱ፡፡ በመድረኩ ላይ ተገኝተው ገለፃ ያደረጉት የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ ህሊና በላቸው (ኢ/ር) ኮርፖሬሽኑ በለውጥ ሂደት ላይ በመሆኑ ሰራተኛው ለሚፈለግበት ለውጥ በመዘጋጀት እራሱን የለውጡ አካል አድርጎ በመስራት ተቋሙ ውጤታማ ሆኖ እንዲቀጥል በመተጋገዝ […]
የቋሚ ንብረት ምዝገባና የሰው ሃብት ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ተግባራዊ ሆነ
ኢምባኮ ህዳር 26/2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ተግባራዊ እያደረገ ባለው የManagement Information System (MIS) ፕሮጀክት ካሉት ሰነዶች/Modules/መካከል የቋሚ ንብረት ምዝገባ እና የሰው ሃብት ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ስርዓት ህዳር 26 ቀን 2016 ዓ.ም ስራ አስጀመረ፡፡ በኮርፖሬሽኑ የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ እና ሰነድ መምሪያ ኃላፊ አቶ ዮሃንስ ተስፋዬ እንደገለፁት በኮርፖሬሽኑ ያሉ ንብረቶችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ አደራጅቶ ለማስቀመጥ ምን […]
በዲዛይን ጥናት ላይ ውይይት ተካሄደ

ኢምባኮ ህዳር 25/03/2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን በዋና መስሪያ ቤቱ ለሚያስገነባው ሁለገብ ማዕከል ህንፃ እየተጠና ባለው ዲዛይን ላይ ከኮርፖሬሽኑ የስራ ኃላፊዎችና የጥናት ቡድን ጋር ህዳር 25 ቀን 2016 ዓም በኮርሬሽኑ የስብሰባ አዳራሽ ውይይት አካሄደ፡፡ ጥናቱ የተዘጋጀው China Rail Transit Engineering Consultancy (CRTEC) በተባለ አማካሪ ድርጅት የተዘጋጀ ሲሆን የዲዛይን፣ የቴክኒክ እና የፋይናንስ ፍላጎት በዝርዝር ቀርቧል፡፡ […]