Ethiopian Railways Corporation

ዘመናዊ የፋይናስ አሰራር ስርዓት ትግበራ ተጀመረ

/ኢምባኮ 21/01/2016ዓ.ም/  ኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ስርዓት በፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት የስራ ዘርፍ መስከረም 21 ቀን 2016 ዓ.ም አስጀመረ፡፡ የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ ህሊና በላቸው (ኢ/ር) በማስጀመሪያ ስነ-ስርዓቱ ላይ ተገኝተው የተቋሙ ክንውኖች በመረጃ አያያዝ ሥርዓት በManagement Information System (MIS) የታገዘ እንዲሆን ለማድረግ ሲከናወን የነበረው ጥናት ተጠናቆ እዚህ በመድረሱ ስራዎች በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ወጥነት ባለው […]

ኮርፖሬሽኑ የጳጉሜ ቀናትን በልዩ ልዩ ኘሮግራሞች አከበረ

/ኢምባኮ 03/13/2015 ዓ.ም/  የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ሰራተኞች እና የስራ ኃላፊዎች የ2016 አዲስ አመት ዋዜማን አስመልክቶ የጳጉሜን ቀናት በልዩ ልዩ ኘሮግራሞች አከበሩ፡፡ የኮርፖሬሽኑን የ2015 በጀት አፈጻጸም እና የ2016 በጀት አመት ዕቅድ በኮርፖሬሽኑ የባቡር ኔትወርክ ስራ አስፈፃሚ ኢ/ር ስለሢ ካሻ ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል፡፡ በዚህ ወቅት የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢ/ር ህሊና በላቸው በሠጡት የሥራ አቅጣጫ በ2015 […]

ኮርፖሬሽኑ ለመቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር የገንዘብ ድጋፍ አደረገ

ሐምሌ 19/2015 ዓ.ም (ኢምባኮ) የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የስራ ኃላፊዎች በመቄዶንያ የአረጋዊያንና አዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል በመገኘት የ300 ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍ አደረገ፡፡ ድጋፉን አስመልክቶ የመቄዶንያ በጎ አድራጎት ማህበር መስራች የክብር ዶክተር ቢኒያም በለጠ ‹‹በማዕከሉ ተገኝቶ ህሙማንን መጎብኘት ከእርዳታው በላይ ትልቅ ተግባር መሆኑን ገልፀው ዛሬ በዚህ ቦታ ተገኝታችሁ በርካታ ህሙማንን በመጎብኘታችሁ “ታምሜ ጠይቃችሁኛል”? የሚለውን ታላቁን […]

የህፃናት ማቆያ ማዕከል ተመረቀ

(ኢምባኮ፡- ሐምሌ 13/2015ዓ.ም) የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን እድሜያቸው ለትምህርት ያልደረሱ የኮርፖሬሽኑ ሰራተኞች ልጆች (ህፃናት) ማቆያ ማዕከል ሐምሌ 13 /2015 ዓ.ም አስመረቀ፡፡ በተሻሻለው የፌደራል መንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010 ሴት የመንግስት ሰራተኞች በመውለዳቸው ምክንያት በስራቸው ላይ ውጤታማ እንዳይሆኑ የሚፈጥርባቸውን እንቅፋት በማስወገድ ያለ ምንም ስጋት እና ሀሳብ በሙሉ ኃይላቸው፣ ጉልበታቸው፣ እውቀታቸው እና ጊዜያቸው ተጠቅመው የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ […]

በአንድ ጀምበር 500 ሚሊዮን ችግኝ የመትከል መርሃ-ግብር ተካሄደ

ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ/ም (ኢምባኮ) የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ማኔጅመንትና እና ሰራተኞች በጋራ በመሆን በአንድ ጀምበር የ500 ሚሊዮን የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብርን በተመለከተ ሐምሌ 10 2015 ዓ.ም ዕለት በዋናው መሥሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ አሻራቸውን አኑረዋል፡፡ ሀገር አቀፍ የችግኝ ተከላ የንቅናቄ መርሃ ግብር ‹‹ነገን ዛሬ እንትከል!›› በሚል መሪ ቃል ተግባረዊ ሲሆን ኮርፖሬሽኑ የዚሁ ፕሮግራም አንድ […]

የManagement Information System (MIS) ስልጠና ለኮርፖሬሽኑ ባለሙያዎች የካቲት 22 ቀን 2015 ዓ.ም በኮርፖሬሽኑ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የስልጠና ማዕከል ተጀመረ፡፡

የስልጠናውን መጀመር አስመልክተው የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ተወካይ  ጌቱ ግዛው(ኢ/ር) ባደረጉት ንግግር  የስልጠናው ዋና አላማ የኮርፖሬሽኑን አሰራር ዘመናዊ በማድረግ ከወረቀት ነፃ የሆነ ፈጣን የመረጃ አያያዝ እና ልውውጥ ስርዓትን ለማስፈን መሆኑን ገልፀው ሰልጣኞች ለስልጠናው ትኩረት ሰጥተው መከታተል እንዳለባቸው እና ከሰለጠኑ በኋላ በየስራ ክፍላቸው ያሉ ባለሙያዎችን በማሰልጠን ወደ ትግበራ ስርአት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ በኮርፖሬሽኑ የአይ.ሲቲ እና ሰነድ መምሪያ […]

የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢ/ር ህሊና በላቸው በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር ሬሚ ማርቹክስ ጋር ተወያዩ፡፡

ውይይቱ ሁለቱ ሀገራት አብሮ ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት መሠረት ያደረገ ሲሆን የፈረንሳይ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በባቡር መሠረተ ልማት፤በባቡር ትራንስፖርት እንዲሁም በሎጂስቲክስ እና መልቲ ሞዳል ስራዎች ላይ መሰማራት በሚችሉበት ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡ በመልቲ ሞዳል ስራዎች ላይ የተሰማሩ የፈረንሳይ ተቋማት በኢትዮጵያ ሊሳተፉ በሚችሉበት ሁኔታ፤በሀገራችን በቀጣይ ሊገነቡ በእቅድ በተያዙ የባቡር መሠረተ ልማቶች መንግስት ባስቀመጣቸው አማራጮች ላይ፤በተለያዩ የፋይናንስ አማራጮች ከተለያዩ የኢትዮጵያ […]