Ethiopian Railways Corporation

የካቲት 30/2017 ዓ.ም (ኢምባኮ)
የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የስራ መሪዎች በባቡር ኢንስቲትዩት አዘጋጅነት በአፍሪካ የአመራር ልህቀት አካዳሚ Building Financial and Operational Resilience in Leadership, Effective Communication and Stakeholder Engagement እና Strategic Leadership and Management Innovation, Critical Thinking, and Decision-Making በሚሉ ርዕሶች ላይ ያተኮረ ስልጠና ተካሂዷል፡፡

ስልጠናው በኮርፖሬሽኑ ያለውን የስልጠና ፍላጎት ታሳቢ በማድረግ በአሁኑ ወቅት ኮርፖሬሽኑ ከባቡር መሠረተ ልማት ግንባታ ባሻገር የተለያዩ የቢዝነስ ዩኒቶችን ከፍቶ ዘርፈ ብዙ ስራ እየሰራ መሆኑንና እንደዚህ ያሉ ሥልጠናዎች ለሥራው አጋዥ በመሆናቸው ከሥልጠናው ከሚገኝ ግብዓት ራስን በማብቃት ውጤታማ ለመሆን የሚያስችል መሆኑን የኮርፖሬሽኑ የባቡር ኢንስቲትዩት ቺፍ ኦፊሰር አቶ በቀለ አጦ ተናግረዋል፡፡

የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዝዳንት አቶ ዛዲግ አብርሃ ውጤታማ ኮሙዩኒኬሽን በተመለከተ በሰጡት ስልጠና ኮሙዩኒኬሽን ለተቋም ስኬትም ሆነ ውድቀት ቀዳሚ መንስኤ መሆኑን ገልጸው በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች የዳበረ የኮሙዩኒኬሽን ክህሎት የሚያስፈልጋቸው መሆኑን በተቋም ውስጥ የሚኖረውን የተግባቦት ሂደት ትኩረት በመስጠት ኮሙዩኒኬሽን መልዕክት ማስተላለፍ ብቻ ሳይሆን መልዕከቱ በተፈለገው መጠን ውጤት ማምጣቱን መገንዘብ እንደሚገባ እንዲሁም በውሳኔ አሰጣጥ ወቅት የሥራ መሪዎች ሊከተሏቸው የሚገቡ ዋና ዋና ነጥቦችን በዝርዝር አብራርተዋል፡፡

በማጠቃለያው ላይ ንግግር ያደረጉት የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ህሊና በላቸው (ኢ/ር) ሥልጠናው የሥራ መሪዎች በየሥራ ዘርፋቸው በውሳኔ ሰጭነት ረገድ ይበልጥ ውጤታማ ለመሆን፣ የተቋሙን የውስጥ ኮሙኒኬሽን ሥርዓታችንን ይበልጥ ለማዘመን እና ፋይናንስን በተመለከተ አዳዲስ የቢዝነስ ሀሳቦችን ለማስፈጸም ሥልጠናው ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ጠቁመው በቀጣይም ከአካዳሚው ጋር በጋራ ለመስራት ሁኔታዎች እንደሚመቻቹ ገልጸዋል፡፡

 

 

ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፤
ድረ  ገፃችንንም ይጎብኙ:  www.erc.gov.et

 

 

 

 

 

 

 



Leave a Reply