Ethiopian Railways Corporation

መጋቢት 5/2017 (ኢምባኮ)

የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን ለኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ኢትዮ ሬይል ሎጀስቲክስ ኃ/የተ/ የግል ማኀበር በሚል ስያሜ መጋቢት 5 ቀን 2017 ዓ.ም በተከናወነው ሥነ ሥርዓት ላይ የመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት ኦኘሬተርነት አከናዋኝ ፈቃድ ሰጠ፡፡

በሥነ ሥርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ህሊና በላቸው ተገኝተው ፈቃዱን ተቀብለዋል፡፡

በፈቃድ ርክክብ ወቅት የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ክቡር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) ድርጅቶቹ ኃላፊነታቸውን በሙያዊ ብቃት እንዲወጡ አሳስበዋል፤ አያይዘውም የሎጅስቲክስን ወሳኝ ሚና በመግለጽ የአገሪቱን ኢኮኖሚያዊ ብቃት በማጎልበት ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነትን በማሳደግ፣ ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንትን በመሳብ እና የንግድ ፍሰቶችን በማስፋፋት ረገድ ያለውን ፋይዳ የገለጹ ሲሆን ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ እንዲሁም የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን አስፈላጊውን ድጋፍና ትብብር እንደሚያደርግ ጠቁመዋል፡፡

ኮርፖሬሽኑ አሁን ባለበት የለውጥ ጐዳና ይህ የመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት ኦኘሬተርነት ፈቃድ ማግኘት በሎጀስቲክስ ዘርፉ ለሀገራችን የወጭ እና ገቢ ንግድ እንቅስቀሴ የበኩሉን ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል፡፡

 

 

ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፤
ድረ  ገፃችንንም ይጎብኙ:  www.erc.gov.et

 

 

 

 

 

 

 



Leave a Reply