Ethiopian Railways Corporation

ሚያዝያ 9 ቀን 2017 ዓ.ም (ኢምባኮ)

============
የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ማኔጅመንትና ሰራተኞች በ2017 በጀት ዓመት የማክሮ ኢኮኖሚ እና ዘርፎች የዘጠኝ ወር እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ዙሪያ ውይይት አካሄዱ ።

በውይይቱ መክፈቻ ወቅት የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ህሊና በላቸው (ኢ/ር) የማክሮ የኢኮኖሚ እና የዘርፎች የዘጠኝ ወር እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እንደሀገር በአፈጻጸም ደረጃ የተገኙ ስኬቶች፣ ያጋጠሙ ችግሮች፣ ለችግሮቹ የተወሰዱ የመፍትሔ እርምጃዎች እና በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ የጋራ መግባባት ለመፍጠር እንዲሁም ኮርፖሬሽኑ ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ እያበረከተ ያለውን አስተዋፅኦ በመረዳት ቀጣይ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ እንደሚረዳ ተናግረዋል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚ አያይዘውም ሪፖርቱ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ትግበራ እና በተለያዩ መስኮች ማለትም አለማቀፍ የኢኮኖሚ አዝማሚያና በኢትዮጵያ ያለው አንድምታ፣ የኢኮኖሚ ሪፎርም ውጤቶችና አዝማሚያዎች እንዲሁም የዋና ዋና ፕሮጀክቶች አፈፃፀምን የያዘ በመሆኑ እንደ ሀገር ያስመዘገብናቸው ስኬቶች፣ የውጭ ምንዛሬያችን ያለበት ደረጃ፣ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብና የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶችን አፈፃፀም የምናይበት እና በኮርፖሬሽናችን ደረጃ ደግሞ ድርሻችን ምን እንደሚመስል አመላካች መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

የ2017 በጀት ዓመት በተቋም ደረጃ ከያዝነው እቅድ ውስጥ ምን ያህሉን አሳክተናል? ቁልፍ የአፈፃፀም አመላካች (KPI) ምን ይመስላል? የፋይናንስ አፈጻጸም የአቅም ግንባታ ሥራዎቻችን እና የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫን የሚያመላክት የስራ ክፍሎች የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በዝርዝር ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል፡፡

በውይይቱ ወቅት ኮርፖሬሽኑ የእቅድ አፈጻጸሙን በጋራ በመገምገም በቀጣይ ለሚታቀደው ዕቅድ በግብአትነት በመውሰድና በማካተት የጋራ ለማድረግ እንዲያስችል ሁሉም የኮርፓሬሽኑ አመራር እና ሰራተኛ የሥራው ባለቤት በመሆኑ በአፈጻጸም ላይ ይበልጥ ትኩረት ሊያደርግበት እንደሚገባ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አሳስበዋል፡፡

በማጠቃለያው ወቅት ከተሳታፊዎች የተለያዩ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

 

 

ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፤
ድረ  ገፃችንንም ይጎብኙ:  www.erc.gov.et

 

 

 

 

 

 

 



Leave a Reply