Ethiopian Railways Corporation

 

የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ባቡር ኢንስቲትዩት በትምህርትና ስልጠና መምሪያ አስተባባሪነት የሙያ፣ ጤና እና ደህንነት አያያዝ ስርዓት (Occupational Health & Safety Management System ISO 45001-2018) ከኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት ጋር በመሆን ከሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች ለተውጣጡ የኮርፖሬሽኑ ሰራተኞች ስልጠና ተሰጠ፡፡
ስልጠናው የስራ ቦታ ደህንነት ትኩረት የሚሻ ጉዳይ እንደመሆኑ የስራ ላይ ጤናና ደህንነት ማኔጅመንት ሲስተምን ፅንሰ ሃሳብ ምንነትን በመገንዘብ በስራ ላይ የሚከሰቱ አደጋዎችን በመከላከል ደህንነቱ የተጠበቀ የስራ አካባቢ ለመፍጠር የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል፡፡
የስራ አካባቢ ደህንነትን ባለመጠበቅ የተነሳ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የሆነ የሰው ህይወት መጥፋት ከማስከተሉም ባሻገር ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውስ መፈጠሩን የተለያዩ ጥናቶች የሚያመለክቱ መሆኑን ስልጠናውን የሰጡት የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት የአካባቢ ደህንነት ደረጃዎች የስልጠናና ቴክኒክ ድጋፍ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ አሸናፊ በቀለ ገልፀዋል
የISO መሰረታዊ ፅንሰ ሃሳብ ምንነት፣ የስራ ጤና እና ደህንነት አስተዳደር ስርዓት መሰረታዊ ጉዳዮች፣ የ ISO 45001 መስፈርቶች፣ የስራ ጤና እና ደህንነት አስተዳደር ስርዓት ሰነዶች እና አተገባበራቸው ምን ይመስላል? የሚሉት የስልጠናው አጠቃላይ የትኩረት ነጥቦች መሆናቸው ተገልጿል፡፡
ከልዩ ልዩ የሥራ ክፍሎች የተውጣጡ አስራ አምስት ባለሙያዎች ተሳታፊ የሆኑበት ይኸው ሥልጠና ለቀጣይ ተከታታይ አምስት ቀናት የሚሰጥ መሆኑም ተገልጿል፡፡

ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፤
ድረ  ገፃችንንም ይጎብኙ:  www.erc.gov.et

 

 

 

 

 

 

 



Leave a Reply