Ethiopian Railways Corporation

የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች የ2017 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አያት በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ ባቡር ኢንስቲትዪት ስልጠና ማዕከል ሀምሌ 24 ቀን 2017 ዓ.ም አካሄዱ፡፡
በቦታው ተገኝተው መርሃ-ግብሩን ያስጀመሩት የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ ህሊና በላቸው(ኢ/ር) ‹‹በመትከል ማንሰራራት›› በሚል መሪ ቃል በሃገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ የሚገኘው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ተግባራዊ በማድረግ እንደ ሃገርም እንደ ኮርፖሬሽንም በጋራ በመስራት ተቋማችንን ወደ ተሻለ ደረጃ እናደርሳለን ብለዋል፡፡ በተጨማሪም ችግኞችን ከመትከል ባለፈ የተተከሉት ችግኞች ፀድቀው ለፍሬ እስኪበቁ ድረስ ለስራ ክፍሎች ደርሻቸውን ከፋፍሎ በኃላፊነት በመስጠት እንክብካቤ እና ክትትል ማድረግ ተገቢ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
በተከናወነው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር ለምግብነት የሚውሉ የተለያዩ ዝርያዎች ያሏቸው ችግኞች ተተክለዋል፡፡

ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፤
ድረ  ገፃችንንም ይጎብኙ:  www.erc.gov.et

 

 

 

 

 

 

 



Leave a Reply