- September 3, 2025
- Posted by: Tigist desalgn
- Category: ዜና
No Comments

ኢትየጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ሶሻል ኮሚቴ ‘’የባቡር ማህበረሰብ ቀን’’ በሚል መሪ ቃል መጪው አዲስ አመትን አስመልክቶ አመታዊ የሰራተኞች በዓል ነሐሴ 27 ቀን 2017 ዓ.ም አከበሩ፡፡
የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ ህሊና በላቸው/ኢ/ር ኮርፖሬሽናችን በተጠናቀቀው በጀት አመት አዳዲስ የኮንስትራክሽን ስራዎች በመጀመር፣ የሎጂስቲክስ እና የባቡር አካዳሚ ስልጠና ፈቃዶችን በማግኘት እንዲሁም በሌሎች ስራዎች አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡን ጠቅሰው በመጪው አመት ወደ ላቀ ደረጃ ለመሸጋገር በትጋት ይጠበቅብናል የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በዕለቱም የኮርፖሬሽኑ የ2017 በጀት ዓመት ሪፖርት፣የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ እንዲሁም ኢምባኮ ከየት ወዴት በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ፅሁፍ፤ በኮርፖሬሽኑ ሰራተኞች ድጋፍ ለሚደረግላቸው ህጻናት ስጦታ፣ እንዲሁም ከኮርፖሬሽኑ በስራ ለውጥ እና በጡረታ ለተሰናበቱ ሰራተኞች ስጦታ ተበርክቶላቸዋል፡፡
ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፤
ድረ ገፃችንንም ይጎብኙ: www.erc.gov.et