- September 12, 2025
- Posted by: Tigist desalgn
- Category: ዜና

መስከረም 2 ቀን 2018 ዓ.ም
የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን እና የጣሊያኑ ኮይፓ ኤ.ስ.ፒ.ኤ. ኢኮኖሚያዊ ትስስርን የሚያጠናክር ፣ በባቡር መሠረተ ልማት እና ተያያዥ ስራዎች ላይ ያተኮረ ስትራቴጂካዊ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ተፈራርሙል።
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ክቡር ዶ./ር አለሙ ስሜ በሁለቱ ሀገሮች መካከል የተደረገው ስምምነት ከባቡር መሰረት ልማት በተጨማሪም ለቴክኖሎጂ ሽግግር እና ለጋራ ብልፅግና ለማረጋገጥ ትልቅ ሚና አለው ብለዋል።
ስምምነቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ለረጅም ጊዜ የቆየውን የጋራ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር የሚያስችል ነው ያሉ ሲሆን የባቡር መሰረተ ልማት የሎጂስቲክስ ስርዓት ለማዘመን እና ቀጠናዊ ትስስርን በመፍጠር የሀገራችን ኢኮኖሚያዊ እድገት ለማፋጠን ትልቅ ድርሻ ይኖረዋል ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሕሊና በላቸው (ኢ/ር) የ ኮይፓ ኢጣሊያ የኢትዮጵያን የባቡር ዘርፍ ራዕይ ለማሳካት በጋራ ለመስራ ያሳየውን ፍላጎት እና ቁርጠኝነት ጠቅሰው ማዕቀፉ የታቀዱ ፕሮጀክቶች ወደ ተግባር በለመወጥ ዘላቂ ልማትን እውን ለማድረግ እንደሚያስችል ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር አጎስቲኖ ፓሌሴ (ዶ/ር) ስምምነቱ በኢትዮጵያ እና በጣሊያን መካከል ያለውን ግንኙነት ያጠናክራል፤ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን እና የጋራ ብልጽግናን ያሻሽላል ብለዋል። ይህ ስምምነት የንግድ አጋርነት ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያና የጣሊያን ዘላቂ ወዳጅነት ምልክት መሆኑን አብራርተው ዘመናዊ፣ ቀልጣፋ እና ቀጣይነት ያለው የባቡር ትራንስፖርት “ለዘላቂ ለኢኮኖሚያዊ ለውጥ እና ቀጠናዊ ውህደት ቁልፍ መሪ ነው” ብለዋል፡፡
የኮይፓ ኢጣሊያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ቪቶ ፋቮሪቶ ሺማሪላ (ዶ/ር) ስምምነቱ ለኮርፖሬሽኑ የረጅም ጊዜ ተቋማዊ አቅምን በመገንባት ፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርን እና የኢንቨስትመንት እድሎችን እንደሚፈጥር ገልፀው የጣሊያኑ ኩባንያ የኢትዮጵያን የባቡር መሠረተ ልማት፣ የሎጂስቲክስ ማዕከላት እና ሌሎች የትራንስፖርት ፕሮጀክቶችን በማልማት ዘርፉን ለማዘመን እንዲሁም አህጉራዊ ውህደትን ለማፋጠን ሚና ይኖረዋል የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን እና ኮይፓ ጣሊያን ኤስ.ፒ.ኤ. ተቋማት በመሰረተ ልማት እና በሀይል ዘርፍ ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ በጋራ ለመስራት ስምምነት ሲፈፅሙ በስራቸው ያሉ ንኡስ ኩባንያዎችም፡-
- ኢንሮስ ላክነር/ Inros Lackner/ – በባቡር ዘርፍ እና በባቡር ምህንድስና ዓለም አቀፍ እውቅና ያለው ኩባንያ ፤
- ሜዲቴክ /MEDTEC /- በባቡር ሀዲድ ጥገና፣ በመገጣጠሚያ፣ በግንባታ እና ሮሊንግስቶክ ጥገና እውቅና ያለው ኩባንያ፣
- አቫንትጋርዴ /AvantGarde/ – በሮሊንግ ስቶክ ጥገና እውቅና ያለው ኩባንያ